መዝ​ሙረ ዳዊት 72:1-20

መዝ​ሙረ ዳዊት 72:1-20 አማ2000

ልባ​ቸው ለቀና ለእ​ስ​ራ​ኤል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ቸር ነው። እኔ ግን እግ​ሮች ሊሰ​ና​ከሉ፥ አረ​ማ​መ​ዴም ሊወ​ድቅ ጥቂት ቀረ። የዐ​መ​ፀ​ኞ​ችን ሰላም አይቼ በኃ​ጥ​ኣን ላይ ቀንቼ ነበ​ርና። ለሞ​ታ​ቸው እረ​ፍት የለ​ው​ምና፤ ለመ​ቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸ​ውም ኀይል የለ​ው​ምና፤ በድ​ካ​ምም ጠላት አል​ሆ​ኑም። ከሰው ጋርም አል​ተ​ገ​ረ​ፉም። ስለ​ዚ​ህም ትዕ​ቢት ያዛ​ቸው፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንና በደ​ላ​ቸ​ውን ተጐ​ና​ጸ​ፉ​አት። መቅን ከቅ​ል​ጥም እን​ደ​ሚ​ወጣ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ይወ​ጣል። ልባ​ቸ​ውም ከት​ዕ​ቢት አለፈ። ዐስ​በው ከንቱ ነገ​ርን ተና​ገሩ። በአ​ር​ያ​ምም ዐመ​ፃን ተና​ገሩ። አፋ​ቸ​ው​ንም በሰ​ማይ አኖሩ፥ አን​ደ​በ​ታ​ቸ​ውም በም​ድር ላይ ተመ​ላ​ለሰ። ስለ​ዚህ ሕዝቤ ወደ​ዚህ ይመ​ለ​ሳሉ፤ ፍጹም ጊዜም በላ​ያ​ቸው ይገ​ኛል፤ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዴት ያው​ቃል? በአ​ር​ያ​ምስ በውኑ የሚ​ያ​ውቅ አለን?” ይላሉ። እነሆ፥ እነ​ዚህ ኃጥ​ኣን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ሁል​ጊ​ዜም ባለ​ጠ​ግ​ነ​ታ​ቸ​ውን ያጸ​ኗ​ታል፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፥ “በውኑ ልቤን በከ​ንቱ አጸ​ደ​ቅ​ሁ​አ​ትን?” እጆ​ቼ​ንም በን​ጽ​ሕና አጠ​ብሁ። ሁል​ጊ​ዜም የተ​ገ​ረ​ፍሁ ሆንሁ፥ መሰ​ደ​ቤም በማ​ለዳ ነው። እን​ደ​ዚህ ብዬ ብና​ገር ኖሮ፥ እነሆ፥ የል​ጆ​ች​ህን ትው​ልድ በበ​ደ​ልሁ ነበር። አው​ቅም ዘንድ ተቀ​በ​ል​ኸኝ፥ ይህ ግን በፊቴ ድካም ነው። ፍጻ​ሜ​አ​ቸ​ውን አውቅ ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ እስ​ክ​ገባ ድረስ፥ ነገር ግን ስለ ሽን​ገ​ላ​ቸው አቈ​የ​ሃ​ቸው፥ በመ​ነ​ሣ​ታ​ቸ​ውም ጣል​ኻ​ቸው። እን​ዴት ለጥ​ፋት ሆኑ! በድ​ን​ገት አለቁ፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ጠፉ። ከእ​ን​ቅ​ልፍ እን​ደ​ሚ​ነቃ፥ አቤቱ፥ በከ​ተ​ማህ ምል​ክ​ታ​ቸ​ውን ታስ​ነ​ው​ራ​ለህ።