የማ​ቴ​ዎስ ወን​ጌል 5:2-11

የማ​ቴ​ዎስ ወን​ጌል 5:2-11 አማ2000

አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ፦ “ንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤መፅናናትን ያገኛሉና። የዋሆች ብፁዓን ናቸው፤ምድርን ይወርሳሉና። ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፤ይጠግባሉና። የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፤ይማራሉና። ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፤እግዚአብሔርን ያዩታልና። የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፤የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና። ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። “ቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች