እንዲህም እያለ ያስተምራቸው ጀመር፤ “በመንፈስ ድኾች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና። የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤ መጽናናትን ያገኛሉና። የዋሆች ብፁዓን ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና። ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፤ ይጠግባሉና። ምሕረት የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤ ምሕረትን ያገኛሉና። ልባቸው ንጹሕ የሆነ ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና። ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና። ስለ ጽድቅ ብለው የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና። “ሰዎች በእኔ ምክንያት ቢሰድቧችሁ፣ ቢያሳድዷችሁና ክፉውን ሁሉ በሐሰት ቢያስወሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።
ማቴዎስ 5 ያንብቡ
ያዳምጡ ማቴዎስ 5
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ማቴዎስ 5:2-11
7 ቀናት
ኢየሱስ ክርስቶስ በብዙ ርዕሶች ላይ አስተምራል ፣ ስለ ዘላለማዊ በረከት ፣ ስለ ዝሙት ፣ ስለ ፀሎት እና ሌሎችሞ ብዙ ርዕሶች አስተሞራል። በዚህ ዘመን ላሉ ሰዎች ይህ ምን ማለት ነው? ምን ትርጉም አለው? ይህ አጭር ቪዲዮ የእያንዳንዱን ቀን የኢየሱስን ክርስቶስን ትምህርት በምሳሌ ይገልፃል::
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች