መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 20:1-3

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 20:1-3 አማ2000

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ በሙሴ ቃል የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁን የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞ​ችን ስጡ። ባለ​ማ​ወቅ ሳይ​ወ​ድድ ሰውን የገ​ደለ በዚያ ይማ​ፀን ዘንድ፥ ለእ​ና​ንተ የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞ​ችን ሥሩ፤ ነፍስ የገ​ደለ ሰውም በአ​ደ​ባ​ባይ ለፍ​ርድ እስ​ኪ​ቀ​ርብ ድረስ በደም ተበ​ቃዩ አይ​ገ​ደል።