ኤፍሬም ከሕዝቡ ጋር ተደባለቀ፤ ኤፍሬም እንዳልተገላበጠ ቂጣ ነው። ጠላት ጕልበቱን በላው፤ እርሱ ግን አላወቀም፤ ሽበትም ወጣበት፤ እርሱም ገና አላስተዋለም። የእስራኤልም ውርደቱና ስድቡ በፊቱ ነው፤ ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ግን አልተመለሱም፤ በዚህም ሁሉ እግዚአብሔርን አልፈለጉትም። ኤፍሬምም ልብ እንደሌላት እንደ ሰነፍ ርግብ ነው፤ ግብፅን ጠሩ፤ ወደ አሦርም ሄዱ። ሲሄዱም አሽክላዬን እዘረጋባቸዋለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎችም አወርዳቸዋለሁ፤ መከራቸውን ሲሰሙ እገሥጻቸዋለሁ። ከእኔ ፈቀቅ ብለዋልና ወዮላቸው! እኔንም ስለ በደሉ ደንግጠዋል! እኔ ታደግኋቸው፤ እነርሱ ግን በሐሰት ተናገሩብኝ። በመኝታቸው ላይ ሆነው ያለቅሱ ነበር እንጂ በልባቸው ወደ እኔ አልጮኹም፤ ስለ እህልና ስለ ወይን ይገዳደሉ ነበር፤ በእኔም ዘንድ ተገሠጹ፤ እኔም ክንዳቸውን አጸናሁ፤ እነርሱ ግን ክፉ ነገርን መከሩብኝ። ወደ ከንቱ ነገር ተመለሱ፤ እንደ ጠማማ ቀስትም ሆኑ፤ አለቆቻቸውም ከምላሳቸው ስንፍና የተነሣ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ይህም በግብፅ ምድር ውስጥ መሳለቂያ ይሆንባቸዋል።
ትንቢተ ሆሴዕ 7 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ሆሴዕ 7:8-16
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች