ትን​ቢተ ሆሴዕ 4:1-7

ትን​ቢተ ሆሴዕ 4:1-7 አማ2000

እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! እው​ነ​ትና ምሕ​ረት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ማወቅ በም​ድር ስለ​ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ይወ​ቅ​ሳ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። ነገር ግን ሐሰት፥ ግዳ​ይና ስር​ቆት፥ ምን​ዝ​ር​ናም ምድ​ርን ሞል​ተ​ዋል፤ ደም​ንም ከደም ጋር ይቀ​ላ​ቅ​ላሉ። ስለ​ዚህ ምድ​ሪቱ ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ በእ​ር​ስ​ዋም ከሚ​ቀ​መጡ ሁሉ ከም​ድር አራ​ዊ​ትና ከሰ​ማይ ወፎች፤ ከም​ድ​ርም ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ጋር ትጠ​ፋ​ለች፤ የባ​ሕ​ሩም ዓሦች ያል​ቃሉ። ነገር ግን ሕዝቤ እን​ደ​ሚ​ከ​ራ​ከር ካህን ነውና እን​ግ​ዲህ የሚ​ከ​ራ​ከር፥ ማንም አይ​ኑር፥ የሚ​ዘ​ል​ፍም ማንም አይ​ኑር። በቀ​ንም ትደ​ክ​ማ​ለህ፤ ነቢ​ዩም ከአ​ንተ ጋር ይደ​ክ​ማል፤ እና​ታ​ች​ሁም ሌሊ​ትን ትመ​ስ​ላ​ለች። ሕዝቤ አእ​ምሮ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ይመ​ስ​ላሉ፤ አን​ተም አእ​ም​ሮህ ተለ​ይ​ቶ​ሃ​ልና እኔ ካህን እን​ዳ​ት​ሆ​ነኝ እተ​ው​ሃ​ለሁ፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ሕግ ረስ​ተ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ልጆ​ች​ህን እረ​ሳ​ለሁ። እንደ ብዛ​ታ​ቸው መጠን ኀጢ​አት ሠሩ​ብኝ፤ እኔም ክብ​ራ​ቸ​ውን ወደ ውር​ደት እለ​ው​ጣ​ለሁ።