ያዕቆብም ዐይኑን አነሣ፤ እነሆም፥ ዔሳውን ሲመጣ አየው፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ ልጆቹንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለቱም ዕቁባቶቹ አደረጋቸው፤ ዕቁባቶቹንና ልጆቻቸውንም በፊት አደረገ፤ ልያንና ልጆችዋን በኋላ፥ ራሔልንና ዮሴፍንም ከሁሉ በኋላ አደረገ። እርሱም በፊታቸው አለፈ፤ ወደ ወንድሙ ወደ ዔሳውም እስኪደርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ። ዔሳውም ሊገናኘው ሮጠ፤ አንገቱንም አቅፎ ሳመው፤ ሁለቱም በአንድነት አለቀሱ። ዔሳውም ዐይኑን አነሣና ሴቶችንና ልጆችን አየ፤ እንዲህም አለ፥ “እነዚህ ምኖችህ ናቸው?” እርሱም፥ “እግዚአብሔር ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለ። ዕቁባቶቹም ከልጆቻቸው ጋር ቀርበው ሰገዱ፤ ደግሞም ልያና ልጆችዋ ቀርበው ሰገዱለት፤ ከዚያም በኋላ ዮሴፍና ራሔል ቀርበው ሰገዱ። ዔሳውም፥ “ያገኘሁት ይህ ሠራዊት ሁሉ ምንህ ነው?” አለ። እርሱም፥ “በጌታዬ ፊት ሞገስን አገኝ ዘንድ ያደረግሁልህ ነው” አለ። ዔሳውም፥ “ለእኔ ብዙ አለኝ፤ ወንድሜ ሆይ፥ የአንተ ለአንተ ይሁን” አለ።
ኦሪት ዘፍጥረት 33 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 33:1-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች