የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 24:1-16

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 24:1-16 አማ2000

በአ​ም​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሊቀ ካህ​ናቱ ሐና​ንያ ከመ​ም​ህ​ራ​ኑና ጠር​ጠ​ሉስ ከሚ​ባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም በአ​ገረ ገዢው ዘንድ ከሰ​ሱት። ጳው​ሎ​ስም በቀ​ረበ ጊዜ ጠር​ጠ​ሉስ እን​ዲህ እያለ ይከ​ስ​ሰው ጀመረ፤ “ክቡር ፊል​ክስ ሆይ፥ በዘ​መ​ንህ ብዙ ሰላ​ምን አግ​ኝ​ተ​ናል፤ በጥ​በ​ብ​ህም በየ​ጊ​ዜው በየ​ሀ​ገሩ የሕ​ዝቡ ኑሮ የተ​ሻ​ሻለ ሆኖ​አል፤ ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም በሁሉ ዘንድ ስት​መ​ሰ​ገን አግ​ኝ​ተ​ና​ታል። ነገር ግን ነገር እን​ዳ​ላ​በ​ዛ​ብህ በአ​ጭሩ ትሰ​ማኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ። ይህን ሰው ሲሳ​ደ​ብና ወን​ጀል ሲሠራ፥ አይ​ሁ​ድ​ንም ሁሉ በየ​ሀ​ገሩ ሲያ​ውክ፥ ናዝ​ራ​ው​ያን የተ​ባ​ሉት ወገ​ኖች የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩ​ት​ንም ክህ​ደት ሲያ​ስ​ተ​ምር አግ​ኝ​ተ​ነ​ዋል። ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም ሊያ​ረ​ክስ ሲሞ​ክር ያዝ​ነው፤ እንደ ሕጋ​ች​ንም ልን​ፈ​ር​ድ​በት ፈል​ገን ነበር። ነገር ግን የሻ​ለ​ቃው ሉስ​ዮስ መጥቶ በብዙ ጭንቅ ከእ​ጃ​ችን ነጥቆ ወደ አንተ ላከው። ከሳ​ሾ​ቹ​ንም ወደ አንተ እን​ዲ​መጡ አዘ​ዛ​ቸው፤ የከ​ሰ​ስ​ን​በ​ት​ንም ነገር ሁሉ መር​ም​ረህ ከእ​ርሱ ልት​ረዳ ትች​ላ​ለህ።” አይ​ሁ​ድም፥ “እው​ነት ነው፤ እን​ዲሁ ነው” ብለው መለሱ። ሀገረ ገዢ​ውም እን​ዲ​ና​ገር ጳው​ሎ​ስን ጠቀ​ሰው፤ ጳው​ሎ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ከብዙ ዘመን ጀምሮ የዚህ ሕዝብ አስ​ተ​ዳ​ዳሪ እንደ ሆንህ አው​ቃ​ለሁ፤ ጠባ​ያ​ቸ​ው​ንም ታው​ቃ​ለህ። አሁ​ንም ደስ እያ​ለኝ ክር​ክ​ሬን አቀ​ር​ባ​ለሁ። እሰ​ግድ ዘንድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ከወ​ጣሁ ዐሥራ ሁለት ቀን እን​ደ​ማ​ይ​ሆን ልታ​ው​ቀው ትች​ላ​ለህ፤ በም​ኵ​ራብ ቢሆን፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ቢሆን፥ በከ​ተ​ማም ቢሆን ሕዝ​ብን ሳውክ፥ ከማ​ንም ጋር ስከ​ራ​ከር አላ​ገ​ኙ​ኝም። በሚ​ከ​ስ​ሱኝ ሁሉ በፊ​ትህ ማስ​ረጃ ማቅ​ረብ አይ​ች​ሉም። ነገር ግን ይህን አረ​ጋ​ግ​ጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ እኔ በሕግ ያለ​ውን፥ በነ​ቢ​ያ​ትም የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ አምኜ እነ​ርሱ ክህ​ደት ብለው በሚ​ጠ​ሩት ትም​ህ​ርት የአ​ባ​ቶ​ችን አም​ላክ አመ​ል​ከ​ዋ​ለሁ። እነ​ር​ሱም ለጻ​ድ​ቃ​ንና ለኃ​ጥ​ኣን የሙ​ታን ትን​ሣኤ ይሆን ዘንድ እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቁ ለእ​ኔም እን​ዲሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ተስፋ አለኝ። እን​ዲሁ እኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በሰው ፊት ሁል​ጊዜ የማ​ታ​ወ​ላ​ውል ሕሊና ትኖ​ረኝ ዘንድ እጋ​ደ​ላ​ለሁ።