መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 14:1-4

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 14:1-4 አማ2000

የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብም የን​ጉሡ ልብ ወደ አቤ​ሴ​ሎም እን​ዳ​ዘ​ነ​በለ ዐወቀ። ኢዮ​አ​ብም ወደ ቴቁሔ ልኮ ከዚያ ብል​ሃ​ተኛ ሴት አስ​መ​ጣና፥ “አል​ቅሺ፤ የኀ​ዘ​ንም ልብስ ልበሺ፤ ዘይ​ትም አት​ቀቢ፤ ስለ ሞተ ሰውም ብዙ ዘመን እን​ደ​ም​ታ​ለ​ቅስ ሴት ሁኚ፤ ወደ ንጉ​ሡም ገብ​ተሽ እን​ዲህ ያለ​ውን ቃል ንገ​ሪው” አላት፤ ኢዮ​አ​ብም ቃሉን በእ​ር​ስዋ አፍ አደ​ረገ። እን​ዲ​ሁም የቴ​ቁ​ሔ​ዪቱ ሴት ወደ ንጉሥ ገብታ በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ላይ ወደ​ቀች፤ ሰግ​ዳም “ንጉሥ ሆይ፥ አድ​ነኝ፤ አድ​ነኝ” አለች።