ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 9:8-12

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 9:8-12 አማ2000

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካ​ሙን ነገር ሁሉ ሊያ​በ​ዛ​ላ​ችሁ ይች​ላል፤ ፍጹም በረ​ከ​ቱ​ንም ለዘ​ወ​ትር ያበ​ዛ​ላ​ችሁ ዘንድ፥ ለሁ​ሉም ታተ​ር​ፉ​ታ​ላ​ችሁ፤ በጎ ሥራ መሥ​ራ​ት​ንም ታበ​ዛ​ላ​ችሁ። “በተነ፤ ለድ​ሃም ሰጠ፤ ጽድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ። እርሱ ዘርን ለዘሪ ይሰ​ጣል፤ እህ​ል​ንም ለም​ግብ ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ ዘራ​ች​ሁ​ንም ያበ​ዛ​ላ​ች​ኋል፤ የጽ​ድ​ቃ​ች​ሁ​ንም መከር ያበ​ጃል። ለብዙ ሰዎች ስለ ሰጣ​ች​ሁም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና በም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ችሁ ልግ​ስና ሁሉ ባለ​ጸ​ጎች ትሆ​ና​ላ​ችሁ። ይህቺ የዚህ ሥራ አገ​ል​ግ​ሎት ግዳጅ የም​ት​ፈ​ጽ​መው ለዚህ ለቅ​ዱ​ሳን ችግር መሟ​ላት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በቅ​ዱ​ሳን ዘን​ድም ደግሞ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና ታበ​ዛ​ለች።