መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ካልእ 9

9
የን​ግ​ሥተ ሳባ ጕዞ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም
(1ነገ. 10፥1-13)
1የሳ​ባም ንግ​ሥት የሰ​ሎ​ሞ​ንን ዝና በሰ​ማች ጊዜ በግ​መ​ሎች ላይ ሽቱና ብዙ ወርቅ፥ የከ​በ​ረም ዕንቍ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የከ​በረ ድን​ጋይ” ይላል። አስ​ጭና ከታ​ላቅ ጓዝ ጋር ሰሎ​ሞ​ንን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በእ​ን​ቆ​ቅ​ልሽ ትፈ​ት​ነው ዘንድ መጣች፤ ወደ ሰሎ​ሞ​ንም በገ​ባች ጊዜ በል​ብዋ ያለ​ውን ሁሉ አጫ​ወ​ተ​ችው። 2ሰሎ​ሞ​ንም የጠ​የ​ቀ​ች​ውን ሁሉ ፈታ​ላት፤ ሰሎ​ሞ​ንም ያል​ፈ​ታው ነገር አል​ነ​በ​ረም። 3የሳ​ባም ንግ​ሥት የሰ​ሎ​ሞ​ንን ጥበብ፥ ሠር​ቶ​ትም የነ​በ​ረ​ውን ቤት፤ 4የማ​ዕ​ዱ​ንም መብል፥ የብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹ​ንም አቀ​ማ​መጥ፥ የሎ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም ሥር​ዐት፥ አለ​ባ​በ​ሳ​ቸ​ው​ንም፥ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹ​ንም፥ አለ​ባ​በ​ሳ​ቸ​ው​ንም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የሚ​ያ​ሳ​ር​ገ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ባየች ጊዜ ተደ​ነ​ቀች። 5ንጉ​ሡ​ንም አለ​ችው፥ “ስለ ነገ​ር​ህና ስለ ጥበ​ብህ በሀ​ገሬ ሳለሁ የሰ​ማ​ሁት ዝና እው​ነት ነው። 6እኔ ግን መጥቼ በዐ​ይኔ እስ​ካ​የሁ ድረስ የነ​ገ​ሩ​ኝን አላ​መ​ን​ሁም፤ እነሆ፥ የጥ​በ​ብ​ህን ታላ​ቅ​ነት እኩ​ሌታ አል​ነ​ገ​ሩ​ኝም፤ በሀ​ገሬ ከሰ​ማ​ሁ​ትም ዝና ይልቅ ጨመ​ር​ህ​ልኝ። 7እነ​ዚህ ሰዎ​ችህ ምስ​ጉ​ኖች ናቸው፤ በፊ​ትህ ሁል​ጊዜ የሚ​ቆ​ሙና ጥበ​ብ​ህን የሚ​ሰሙ እነ​ዚህ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም ምስ​ጉ​ኖች ናቸው። 8በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ንጉሥ እን​ድ​ት​ሆን በዙ​ፋኑ ላይ ያስ​ቀ​ም​ጥህ ዘንድ የወ​ደ​ደህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ይሁን፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያጸ​ና​ቸው ዘንድ ወድ​ዶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ስለ​ዚህ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ታደ​ርግ ዘንድ በላ​ያ​ቸው አነ​ገ​ሠህ።”
9ለን​ጉ​ሡም መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ፥ እጅ​ግም ብዙ ሽቱ፥ የከ​በ​ረም ዕንቍ ሰጠ​ችው፤ የሳ​ባም ንግ​ሥት ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን እንደ ሰጠ​ችው ያለ ሽቱ ከቶ አል​ነ​በ​ረም። 10የኪ​ራም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችና የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ከሴ​ፌር ለሰ​ሎ​ሞን ወርቅ አመጡ፤ የሰ​ን​ደል እን​ጨ​ትና የከ​በረ ዕን​ቍም ደግሞ አመጡ። 11ንጉ​ሡም ከሰ​ን​ደሉ እን​ጨት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና ለን​ጉሡ ቤት ደርብ፥ ለመ​ዘ​ም​ራ​ኑም መሰ​ን​ቆና በገና አደ​ረገ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ያለ በይ​ሁዳ ምድር ከቶ አል​ታ​የም ነበር። 12እር​ስ​ዋም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ካመ​ጣ​ችው የበ​ለጠ፥ ንጉሡ ሰሎ​ሞን የወ​ደ​ደ​ች​ውን ሁሉ፥ ከእ​ር​ሱም የለ​መ​ነ​ች​ውን ሁሉ ለሳባ ንግ​ሥት ሰጣት፤ እር​ስ​ዋም ተመ​ልሳ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችዋ ጋር ወደ ሀገ​ርዋ ሄደች።
የን​ጉሥ ሰሎ​ሞን ሀብት ብዛት
(1ነገ. 10፥14-25)
13በየ​ዓ​መ​ቱም ወደ ሰሎ​ሞን የሚ​መጣ የወ​ርቅ ሚዛን ስድ​ስት መቶ ስድሳ ስድ​ስት መክ​ሊት ወርቅ ነበረ። 14ነጋ​ድ​ራ​ሶ​ችና ነጋ​ዴ​ዎች ከሚ​ያ​መ​ጡት ሌላ የዓ​ረብ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ፥ የም​ድ​ሩም ሹሞች ወደ ንጉሡ ሰሎ​ሞን ወር​ቅና ብር ያመጡ ነበር 15ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን በጥ​ፍ​ጥፍ ወርቅ ሁለት መቶ አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ አሠራ፤ በየ​አ​ን​ዳ​ን​ዱም አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ ውስጥ የገ​ባው የጠራ ወርቅ ስድ​ስት መቶ ሰቅል ነበረ። 16ከጥ​ፍ​ጥ​ፍም ወርቅ ሦስት መቶ ጋሻ አሠራ፤ በየ​አ​ን​ዳ​ን​ዱም ጋሻ የገ​ባው ወርቅ ሦስት መቶ ሰቅል ነበረ፤ ንጉ​ሡም የሊ​ባ​ኖስ ዱር በተ​ባ​ለው ቤት ውስጥ አኖ​ራ​ቸው። 17ንጉ​ሡም ደግሞ ከዝ​ሆን ጥርስ ታላቅ ዙፋን አሠራ፤ በጥሩ ወር​ቅም ለበ​ጠው። 18ወደ ዙፋ​ኑም የሚ​ያ​ስ​ሄዱ፥ በወ​ርቅ የተ​ለ​በጡ ስድ​ስት እር​ከ​ኖች ነበሩ፤ በዚ​ህና በዚያ በመ​ቀ​መ​ጫው አጠ​ገብ ሁለት የክ​ንድ መደ​ገ​ፊ​ያ​ዎች ነበ​ሩ​በት፤ በመ​ደ​ገ​ፊ​ያ​ዎ​ቹም አጠ​ገብ ሁለት አን​በ​ሶች ቆመው ነበር። 19በስ​ድ​ስ​ቱም እር​ከ​ኖች ላይ በዚ​ህና በዚያ ዐሥራ ሁለት አን​በ​ሶች ቆመው ነበር፤ በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ እን​ዲህ ያለ ሥራ አል​ተ​ሠ​ራም። 20ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን የሚ​ጠ​ጣ​በት ዕቃ ሁሉ የወ​ርቅ ነበረ፤ የሊ​ባ​ኖስ ዱር በተ​ባ​ለ​ውም ቤቱ የሚ​ገ​ለ​ገ​ል​በት ዕቃ ሁሉ ጥሩ ወርቅ ነበረ፤ በሰ​ሎ​ሞ​ንም ዘመን ብር ከቶ አይ​ቈ​ጠ​ርም ነበር። 21ለን​ጉ​ሡም ከኪ​ራም አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር ወደ ተር​ሴስ የሚ​ሄዱ መር​ከ​ቦች ነበ​ሩት፤ በሦ​ስት በሦ​ስት ዓመ​ትም አንድ ጊዜ የተ​ር​ሴስ መር​ከ​ቦች ወር​ቅና ብር፥ የዝ​ሆ​ንም ጥር​ስና ዝን​ጀሮ#ዕብ. “ዝን​ጉ​ር​ጉር ወፍም” የሚል ይጨ​ም​ራል። ይዘው ይመጡ ነበር።
22ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ከም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ትና በጥ​በብ በለጠ። 23የም​ድ​ርም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በልቡ ያኖ​ረ​ውን ጥበ​ቡን ይሰሙ ዘንድ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ፊት ሊያዩ ይመኙ ነበር። 24ከእ​ነ​ር​ሱም እያ​ን​ዳ​ንዱ ገጸ በረ​ከ​ቱን፥ የወ​ር​ቅ​ንና የብ​ርን ዕቃ፥ ልብ​ስ​ንና የጦር መሣ​ሪ​ያን፥ ሽቱ​ው​ንም፥ ፈረ​ሶ​ች​ንና በቅ​ሎ​ዎ​ችን እየ​ያዘ በየ​ዓ​መቱ ያመጣ ነበር። 25ሰሎ​ሞ​ንም ለሰ​ረ​ገ​ሎች አራት ሺህ እን​ስት ፈረ​ሶ​ችና#ዕብ. “ለፈ​ረ​ሶ​ችና ለሰ​ረ​ገ​ሎች አራት ሺህ ጋጥ” ይላል። ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞች ነበ​ሩት፤ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ከተ​ሞች፥ ከን​ጉሡ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አኖ​ራ​ቸው። 26ከኤ​ፍ​ራ​ጥ​ስም#“ከኤ​ፍ​ራ​ጥ​ስም” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ምድ​ርና እስከ ግብፅ ዳርቻ ድረስ ባሉ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ነገሠ። 27ንጉ​ሡም ወር​ቁ​ንና ብሩን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ድን​ጋይ፥ የዝ​ግ​ባ​ው​ንም እን​ጨት በቆላ እን​ደ​ሚ​በ​ቅል ሾላ ብዛት አደ​ረ​ገው። 28ለሰ​ሎ​ሞ​ንም ፈረ​ሶች ከግ​ብ​ፅና ከየ​ሀ​ገሩ ሁሉ ይመ​ጡ​ለት ነበር።
29የቀ​ረ​ውም ፊተ​ኛ​ውና ኋለ​ኛው የሰ​ሎ​ሞን ነገር በነ​ቢዩ በና​ታን ታሪክ፥ በሴ​ሎ​ና​ዊ​ውም በአ​ኪያ ትን​ቢት፥ ስለ ናባ​ጥም ልጅ ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ባየው በባለ ራእዩ በኢ​ዩ​ሔል#ዕብ. “አዶ” ይላል። ራእይ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? 30ሰሎ​ሞ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ አርባ ዓመት ነገሠ። 31ሰሎ​ሞ​ንም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ቀበ​ሩት፤ ልጁም ሮብ​ዓም በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ