መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 13
13
የይሁዳ ንጉሥ አብያ ከኢዮርብዓም ጋር ያደረገው ጦርነት
(1ነገ. 15፥1-8)
1ንጉሡም ኢዮርብዓም በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት አብያ በይሁዳ ላይ ንጉሥ ሆነ። 2ሦስት#አንዳንድ የግእዝ ዘርዕ “ስድስት” ይላል። ዓመትም በኢየሩሳሌም ነገሠ፤ የእናቱም ስም መዓካ ነበረ፤ የገባዖን ሰው የኡርኤል ልጅ ነበረች። በአብያና በኢዮርብዓም መካከልም ሰልፍ ነበረ። 3አብያም የተመረጡትን አራት መቶ ሺህ ኀያላን ሰልፈኞች ይዞ ወደ ሰልፍ ወጣ፤ ኢዮርብዓምም የተመረጡትን ስምንት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ይዞ በእርሱ ላይ ተሰለፈ። 4አብያም በኤፍሬም ተራራ ባለው በሳምሮን#ዕብ. “በጽማራይም” ይላል። ተራራ ላይ ቆሞ እንዲህ አለ፥ “ኢዮርብዓምና እስራኤል ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤ 5የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ መንግሥትን ለዳዊትና ለልጆቹ በጨው#“በጨው” የሚለው በግእዝ የለም። ቃል ኪዳን ለዘለዓለም እንደ ሰጠ በውኑ አታውቁምን? 6የዳዊት ልጅ የሰሎሞን አገልጋይ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ግን ተነሥቶ በጌታው ላይ ዐመፀ። 7ክፉዎች ሰዎችና የሕግ ተላላፊዎች ልጆችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሮብዓም ሕፃን በነበረና በልቡ ድፍረት ባልነበረው ጊዜ፥ ሊቋቋመውም ባልቻለበት ጊዜ፥ በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ላይ በረታበት። 8አሁንም በዳዊት ልጆች እጅ የሚሆነውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ልትቋቋሙ እንዲህ ትላላችሁ።#ዕብ. “ታስባላችሁ” ይላል። እናንተም እጅግ ታላቅ ሕዝብ ናችሁ፥ ኢዮርብዓምም አማልክት አድርጎ የሠራላችሁ የወርቅ እንቦሶች ከእናንተ ጋር ናቸው። 9የአሮንን ልጆች የእግዚአብሔርን ካህናትና ሌዋውያን አላሳደዳችሁምን? ከምድርም አሕዛብ ሁሉ ለራሳችሁ ካህናትን አላደረጋችሁምን? አንድ ወይፈንና ሰባት አውራ በጎችን ይዞ ራሱን ይቀድስ ዘንድ የሚመጣ ሁሉ አማልክት ላልሆኑት ለእነዚያ ካህን ይሆናል። 10እኛ ግን አምላካችን እግዚአብሔርን አልተውነውም፤ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች የአሮን ልጆች ካህናቱና ሌዋውያኑ በየሰሞናቸው ያገለግሉታል። 11በየጥዋቱና በየማታውም ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ጣፋጩን ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የገጹንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹንም ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንጠብቃለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል። 12እነሆም፥ እግዚአብሔር በእኛ ላይ አለቃ ነው፤ መለከቱንም የሚነፉ ካህናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፤ በእናንተም ላይ ይጮኻሉ። የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አይበጃችሁምና ከአባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር አቷጉ።”
13ኢዮርብዓም ግን በስተኋላቸው ይመጣባቸው ዘንድ ድብቅ ጦር አዞረባቸው፤ እነርሱ በይሁዳ ሰፈር ፊት ሳሉ ድብቅ ጦሩ በስተኋላቸው ከበባቸው። 14የይሁዳም ሰዎች ወደ ኋላቸው በተመለከቱ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰልፉ በፊታቸውና በኋላቸው ነበረ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ፤ ካህናቱም መለከቱን ነፉ። 15የይሁዳም ሰዎች ጮኹ፤ የይሁዳም ሰዎች በጮኹ ጊዜ እግዚአብሔር ኢዮርብዓምንና እስራኤልን ሁሉ በይሁዳ ንጉሥ በአብያና በሕዝቡ ፊት መታቸው። 16የእስራኤልም ልጆች ከይሁዳ ሰዎች ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔርም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። 17አብያና ሕዝቡም ታላቅ አመታት መቱአቸው፤ ከእስራኤልም አምስት መቶ ሺህ የተመረጡ ሰዎች ተገድለው ወደቁ። 18በዚያም ጊዜ የእስራኤል ልጆች ተዋረዱ፤ የይሁዳም ልጆች በአባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ታምነው ነበርና አሸነፉ። 19አብያም ኢዮርብዓምን ተከትሎ አሳደደው፤ ከእርሱም ከተሞቹን ቤቴልንና መንደሮችዋን፥ ይሳናንና መንደሮችዋን፥ ዔፍሮንንና መንደሮችዋን ወሰደ። 20ኢዮርብዓምም ከዚያ በኋላ በአብያ ዘመን አልበረታም፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው፤ ሞተም። 21አብያም ጸና፤ ዐሥራ አራት ሚስቶችንም አገባ፤ ሃያ ሁለትም ወንዶች ልጆችንና ዐሥራ ስድስት ሴቶች ልጆችን ወለደ። 22የአብያም የቀረው ነገርና አካሄዱ የተናገራቸውም ቃሎች በነቢዩ በአዶ መጽሐፍ ተጽፈዋል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 13: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ