መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 16:7-12

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 16:7-12 አማ2000

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ፊቱን፥ የቁ​መ​ቱ​ንም ዘለ​ግታ አትይ፤ ሰው እን​ደ​ሚ​ያይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ይ​ምና ናቅ​ሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ልብን ያያል” አለው። እሴ​ይም አሚ​ና​ዳ​ብን ጠርቶ በሳ​ሙ​ኤል ፊት አሳ​ለ​ፈው፤ እር​ሱም፥ “ይህን ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​መ​ረ​ጠ​ውም” አለ። እሴ​ይም ሣማ​ዕን አሳ​ለ​ፈው፤ እር​ሱም፥ “ይህን ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​መ​ረ​ጠ​ውም” አለ። እሴ​ይም ከል​ጆቹ ሰባ​ቱን በሳ​ሙ​ኤል ፊት አሳ​ለ​ፋ​ቸው። ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አል​መ​ረ​ጠም” አለው። ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “ልጆ​ችህ እኒህ ብቻ ናቸው?” አለው። እር​ሱም፥ “ታናሹ ገና ቀር​ቶ​አል፤ እነ​ሆም፥ በጎ​ችን ይጠ​ብ​ቃል” አለ። ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “እርሱ እስ​ኪ​መጣ ድረስ ለማ​ዕድ አን​ቀ​መ​ጥ​ምና ልከህ አስ​መ​ጣው” አለው። ልኮም አስ​መ​ጣው፤ እር​ሱም ቀይ፥ ዐይ​ኑም የተ​ዋበ፥ መል​ኩም ያማረ ነበረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ይህ መል​ካም ነውና ተነ​ሥ​ተህ ዳዊ​ትን ቅባው” አለው።