1 ሳሙኤል 16:7-12

1 ሳሙኤል 16:7-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፣ “መልኩን ወይም ቁመቱን አትይ፤ እኔ ንቄዋለሁና። እግዚአብሔር የሚያየው፣ ሰው እንደሚያየው አይደለም። ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው። ከዚያም እሴይ አሚናዳብን ጠርቶ በሳሙኤል ፊት እንዲያልፍ አደረገ፤ ሳሙኤል ግን፣ “እግዚአብሔር ይህንም አልመረጠውም” አለው። እሴይም ሣማን አሳለፈ፤ ሳሙኤልም፣ “እርሱንም እግዚአብሔር አልመረጠውም” አለ። እሴይም ሰባቱን ልጆቹን በሳሙኤል ፊት እንዲያልፉ አደረገ፤ ሳሙኤል ግን፣ “እግዚአብሔር እነዚህንም አልመረጣቸውም” አለው። ቀጥሎም እሴይን፣ “ልጆችህ እነዚሁ ብቻ ናቸውን?” ሲል ጠየቀው። እሴይም፣ “የሁሉም ታናሽ ገና አልመጣም፤ ነገር ግን በጎች እየጠበቀ ነው” ብሎ መለሰ። ሳሙኤልም፣ “በል ልከህ አስመጣው፤ እስኪመጣ ድረስ አንቀመጥምና” አለው። ስለዚህ ልኮ አስመጣው፤ እርሱም ደም ግባት ያለው፣ ዐይኑ የሚያምርና መልከ መልካም ነበረ። እግዚአብሔርም፣ “የመረጥሁት ይህ ነውና ተነሥተህ ቀባው” አለው።

1 ሳሙኤል 16:7-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ፊቱን፥ የቁ​መ​ቱ​ንም ዘለ​ግታ አትይ፤ ሰው እን​ደ​ሚ​ያይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ይ​ምና ናቅ​ሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ልብን ያያል” አለው። እሴ​ይም አሚ​ና​ዳ​ብን ጠርቶ በሳ​ሙ​ኤል ፊት አሳ​ለ​ፈው፤ እር​ሱም፥ “ይህን ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​መ​ረ​ጠ​ውም” አለ። እሴ​ይም ሣማ​ዕን አሳ​ለ​ፈው፤ እር​ሱም፥ “ይህን ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​መ​ረ​ጠ​ውም” አለ። እሴ​ይም ከል​ጆቹ ሰባ​ቱን በሳ​ሙ​ኤል ፊት አሳ​ለ​ፋ​ቸው። ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አል​መ​ረ​ጠም” አለው። ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “ልጆ​ችህ እኒህ ብቻ ናቸው?” አለው። እር​ሱም፥ “ታናሹ ገና ቀር​ቶ​አል፤ እነ​ሆም፥ በጎ​ችን ይጠ​ብ​ቃል” አለ። ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “እርሱ እስ​ኪ​መጣ ድረስ ለማ​ዕድ አን​ቀ​መ​ጥ​ምና ልከህ አስ​መ​ጣው” አለው። ልኮም አስ​መ​ጣው፤ እር​ሱም ቀይ፥ ዐይ​ኑም የተ​ዋበ፥ መል​ኩም ያማረ ነበረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ይህ መል​ካም ነውና ተነ​ሥ​ተህ ዳዊ​ትን ቅባው” አለው።

1 ሳሙኤል 16:7-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፣ “መልኩን ወይም ቁመቱን አትይ፤ እኔ ንቄዋለሁና። እግዚአብሔር የሚያየው፣ ሰው እንደሚያየው አይደለም። ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው። ከዚያም እሴይ አሚናዳብን ጠርቶ በሳሙኤል ፊት እንዲያልፍ አደረገ፤ ሳሙኤል ግን፣ “እግዚአብሔር ይህንም አልመረጠውም” አለው። እሴይም ሣማን አሳለፈ፤ ሳሙኤልም፣ “እርሱንም እግዚአብሔር አልመረጠውም” አለ። እሴይም ሰባቱን ልጆቹን በሳሙኤል ፊት እንዲያልፉ አደረገ፤ ሳሙኤል ግን፣ “እግዚአብሔር እነዚህንም አልመረጣቸውም” አለው። ቀጥሎም እሴይን፣ “ልጆችህ እነዚሁ ብቻ ናቸውን?” ሲል ጠየቀው። እሴይም፣ “የሁሉም ታናሽ ገና አልመጣም፤ ነገር ግን በጎች እየጠበቀ ነው” ብሎ መለሰ። ሳሙኤልም፣ “በል ልከህ አስመጣው፤ እስኪመጣ ድረስ አንቀመጥምና” አለው። ስለዚህ ልኮ አስመጣው፤ እርሱም ደም ግባት ያለው፣ ዐይኑ የሚያምርና መልከ መልካም ነበረ። እግዚአብሔርም፣ “የመረጥሁት ይህ ነውና ተነሥተህ ቀባው” አለው።

1 ሳሙኤል 16:7-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ግን “የኤሊአብን ቁመት መርዘምና መልከ ቀናነቱን አትይ፤ እኔ እርሱን አልፈለግሁትም፤ እኔ የምፈርደው ሰዎች እንደሚፈርዱት አይደለም፤ ሰው የውጪ መልክን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው። ከዚህ በኋላ እሴይ አቢናዳብ ተብሎ የሚጠራውን ልጁን ወደ ሳሙኤል አመጣለት፤ ሳሙኤል ግን “እግዚአብሔር ይህኛውንም አልመረጠውም” አለ። ቀጥሎም እሴይ ሻማ ተብሎ የሚጠራውን ልጁን አመጣ፤ ሳሙኤል ግን “እግዚአብሔር ይህኛውንም አልመረጠም” አለ። በዚህም ዐይነት እሴይ ሰባቱንም ልጆቹን አቅርቦ በሳሙኤል ፊት አሰለፋቸው፤ ሳሙኤልም እሴይን “እነሆ፥ ከእነዚህ መካከል እግዚአብሔር አንዱንም አልመረጠም” አለው። “ታዲያ ሌሎች ልጆች የሉህምን?” ሲል ጠየቀው። እሴይም “የሁሉ ታናሽ የሆነ አንድ ልጅ አለ፤ እርሱ ግን ወደ በግ እረኝነት ሄዶአል” ሲል መለሰለት። ሳሙኤልም “እርሱን አስጠርተህ አምጣው፤ እርሱ ሳይመጣ መሥዋዕት አናቀርብም” አለው። ስለዚህም እሴይ ልኮ አስጠራው፤ እርሱ ቀይ፥ መልከ መልካምና ዐይኖቹ የሚያበሩ ጤናማ ወጣት ነበር፤ እግዚአብሔርም ሳሙኤልን “የመረጥኩት ሰው ይህ ነውና ተነሥተህ እርሱን ቀባው!” አለው።

1 ሳሙኤል 16:7-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጌታ ግን ሳሙኤልን፥ “መልኩን ወይም ቁመቱን አትይ፤ እኔ ንቄዋለሁና። ጌታ የሚያየው፥ ሰው እንደሚያየው አይደለም። ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል፤ ጌታ ግን ልብን ያያል” አለው። ከዚያም እሴይ አሚናዳብን ጠርቶ በሳሙኤል ፊት እንዲያልፍ አደረገ፤ ሳሙኤል ግን፥ “ጌታ ይህንንም አልመረጠውም” አለው። እሴይም ሻማን አሳለፈ፤ ሳሙኤልም፥ “እርሱንም ጌታ አልመረጠውም” አለ። እሴይም ሰባቱን ልጆቹን በሳሙኤል ፊት እንዲያልፉ አደረገ፤ ሳሙኤል ግን፥ “ጌታ እነዚህንም አልመረጣቸውም” አለው። ቀጥሎም እሴይን፥ “ልጆችህ እነዚሁ ብቻ ናቸውን?” ሲል ጠየቀው። እሴይም፥ “የሁሉም ታናሽ ገና አልመጣም፤ ነገር ግን በጎች እየጠበቀ ነው” ብሎ መለሰ። ሳሙኤልም እሴይን፥ “በል ልከህ አስመጣው፤ እስኪመጣ ድረስ አንቀመጥም” አለው። ስለዚህ ልኮ አስመጣው፤ እርሱም ደም ግባት ያለው፥ ዐይኑ የሚያምርና መልከ መልካም ነበረ። ጌታም፥ “የመረጥሁት ይህ ነውና ተነሥተህ ቀባው” አለው።

1 ሳሙኤል 16:7-12

1 ሳሙኤል 16:7-12 NASV