መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 8
8
የብንያም ትውልድ
1ብንያምም በኵሩን ቤላን፥ ሁለተኛውንም አስቤልን፥ ሦስተኛውንም አሐራን፤ 2አራተኛውንም ኖሐን፥ አምስተኛውንም ራፋን ወለደ። 3ለቤላም ልጆች ነበሩት፤ አዳር፥ ጌራ፥ አቤሁድ፤ 4አቤሱ፥ ናዕማን፥ አሖዋ፤ 5ጌራ፥ ሰፉፋም፥ ሑራም።#ግእዙ “አኪራን” ይላል። 6እነዚህ የኤሁድ ልጆች ናቸው፤ እነዚህ በጌባ የሚቀመጡ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ናቸው፤ ወደ መነሐትም ተማረኩ፤ 7ናዕማን፥ አኪያ፥ ጌራ፥ እነርሱም ተማረኩ። ዖዛንና አሂሑድን ወለደ። 8ሰሐራይምም ሚስቶቹን ሑሴምንና በዕራን ከሰደደ በኋላ በሞዓብ ሜዳ ልጆችን#ግእዙ “ሞዓብን በምድረ በዳ ወለደ” ይላል። ወለደ። 9ከሚስቱ ከሖዲሽ ዮባብን፥ ዲብያን፥ ማሴን፥ ማልካምን፤ 10ኢያሱብን፥ ሻክያን፥ ሜርማን ወለደ። እነዚህም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች ነበሩ። 11ከሑሲምም አቢጡብንና ኤልፍዓልን ወለደ። 12የኤልፍዓልም ልጆች ዖቤድ፥ ሚሳም፥ ኦኖንና ሎድን፥ መንደሮቻቸውንም የሠራ ሳሜር፤ 13በሪዓ፥ ሰማዕ ነበሩ፤ እነርሱም የጌትን ነዋሪዎች ያሳደዱ የኤሎን ሰዎች የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤ 14ወንድሞቹም ሶሲቅና ይሬሞት፤ 15ዝባድያ፥ ዓራድ፥ ዔዴር፤ 16ሚካኤል፥ የሴፋ፥ ዮሐ፥ የበሪዓም ልጆች፤ 17ዝባድያ፥ ሜሱላም፥ ሕዝቂ፥ ሔቤር፤ 18ይሰምራይ፥ ይዝሊያ፥ ዮባብ፥ 19የኤልፍዓል ልጆች ያቂም፥ ዝክሪ፥ ዘብዲ፥ 20ኤሊዔናይ፥ ጼልታይ፥ ኤሊኤል፤ 21ዓዳያ፥ ብራያ፥ ሲምራት፥ የሰሜኤ ልጆች፤ 22ይሰጳን፥ ዖቤድ፥ ኤሊኤል፤ 23ዓብዶን፥ ዝክሪ፥ ሐናን፤ 24ሐናንያ፥ አንበሪ፥ ኤላም፤ አናቶትያ፥ 25ይቲን፥ ይፍዴያ፥ ፋኑኤል፥ የሶሴቅ ልጆች፤ 26ሸምሸራይ፥ ሸሃሪያ፥ ጎቶልያ፤ 27ያሬሽያ፥ ኤልያስ፥ ዝክሪ፥ የይሮሐም ልጆች። 28እነዚህ በትውልዶቻቸው አለቆች ነበሩ፤ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤ እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።
29የገባዖን አባት በገባዖን ይኖር ነበር#አንዳንድ የዕብ. ዘር “የገባዖን አባት ይኢዔል” ይላል። የሚስቱም ስም መዓካ ነበር፤ 30የበኵር ልጁ ዓብዶን፥ ሱር፥ ቂስ፥ በኣል፥ ኔር፥ ናዳብ፥ 31ጌዶርና፥ ወንድሙ ዛኪር ሜቅሎት፤ 32ሜቅሎትም ሳምአን ወለደ፤ እነርሱ ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ተቀመጡ።
የንጉሥ ሳኦል ትውልድ
33ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሜልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስበኣልን ወለደ። 34የዮናታንም ልጅ መሪበኣል ነበረ፤ መሪበኣልም ሚካን ወለደ። 35የሚካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓ፥ አካዝ ነበሩ። 36አካዝም ይሆዓዳን ወለደ፤ ይሆዓዳም ዓሌሜትን፥ ዓዝሞትን፥ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ማሴዕን ወለደ። 37ማሴዕም በዓናን ወለደ፤ ልጁም ራፋያ ነበረ፤ ልጁ ኤልዓሣ፥ ልጁ ኤሴል፤ 38ለኤሴልም ስድስት ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ይህ ነበረ፤ ዓዝሪቃም፥ በኬርዩ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቦኬርዮ” በኵሩ ብሎ ለአዘረቃም ይቀጥልና 6ኛ አሣ የሚል ይጽፋል ግእዙ 5 ብቻ ይጽፋል። እስማኤል፥ ሰዓርያ፥ አብድዩ፥ ሐናን፤ እነዚህ ሁሉ የአሴል ልጆች ነበሩ። 39የወንድሙም የአሴል ልጆች፤ በኵሩ ኡላም፥ ሁለተኛውም ኤያስ፥ ሦስተኛውም ኤሊፋላት። 40የኡላም ልጆች ጽኑዓን ኀያላንና ቀስተኞች ነበሩ፤ ለእነርሱም መቶ አምሳ የሚያህሉ ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩአቸው፤ እነዚህ ሁሉ የብንያም ልጆች ነበሩ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 8: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ