መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ቀዳ​ማዊ 8

8
የብ​ን​ያም ትው​ልድ
1ብን​ያ​ምም በኵ​ሩን ቤላን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም አስ​ቤ​ልን፥ ሦስ​ተ​ኛ​ው​ንም አሐ​ራን፤ 2አራ​ተ​ኛ​ው​ንም ኖሐን፥ አም​ስ​ተ​ኛ​ው​ንም ራፋን ወለደ። 3ለቤ​ላም ልጆች ነበ​ሩት፤ አዳር፥ ጌራ፥ አቤ​ሁድ፤ 4አቤሱ፥ ናዕ​ማን፥ አሖዋ፤ 5ጌራ፥ ሰፉ​ፋም፥ ሑራም።#ግእዙ “አኪ​ራን” ይላል። 6እነ​ዚህ የኤ​ሁድ ልጆች ናቸው፤ እነ​ዚህ በጌባ የሚ​ቀ​መጡ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች ናቸው፤ ወደ መነ​ሐ​ትም ተማ​ረኩ፤ 7ናዕ​ማን፥ አኪያ፥ ጌራ፥ እነ​ር​ሱም ተማ​ረኩ። ዖዛ​ንና አሂ​ሑ​ድን ወለደ። 8ሰሐ​ራ​ይ​ምም ሚስ​ቶ​ቹን ሑሴ​ም​ንና በዕ​ራን ከሰ​ደደ በኋላ በሞ​ዓብ ሜዳ ልጆ​ችን#ግእዙ “ሞዓ​ብን በም​ድረ በዳ ወለደ” ይላል። ወለደ። 9ከሚ​ስቱ ከሖ​ዲሽ ዮባ​ብን፥ ዲብ​ያን፥ ማሴን፥ ማል​ካ​ምን፤ 10ኢያ​ሱ​ብን፥ ሻክ​ያን፥ ሜር​ማን ወለደ። እነ​ዚ​ህም ልጆች የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ነበሩ። 11ከሑ​ሲ​ምም አቢ​ጡ​ብ​ንና ኤል​ፍ​ዓ​ልን ወለደ። 12የኤ​ል​ፍ​ዓ​ልም ልጆች ዖቤድ፥ ሚሳም፥ ኦኖ​ንና ሎድን፥ መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም የሠራ ሳሜር፤ 13በሪዓ፥ ሰማዕ ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም የጌ​ትን ነዋ​ሪ​ዎች ያሳ​ደዱ የኤ​ሎን ሰዎች የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች ነበሩ፤ 14ወን​ድ​ሞ​ቹም ሶሲ​ቅና ይሬ​ሞት፤ 15ዝባ​ድያ፥ ዓራድ፥ ዔዴር፤ 16ሚካ​ኤል፥ የሴፋ፥ ዮሐ፥ የበ​ሪ​ዓም ልጆች፤ 17ዝባ​ድያ፥ ሜሱ​ላም፥ ሕዝቂ፥ ሔቤር፤ 18ይሰ​ም​ራይ፥ ይዝ​ሊያ፥ ዮባብ፥ 19የኤ​ል​ፍ​ዓል ልጆች ያቂም፥ ዝክሪ፥ ዘብዲ፥ 20ኤሊ​ዔ​ናይ፥ ጼል​ታይ፥ ኤሊ​ኤል፤ 21ዓዳያ፥ ብራያ፥ ሲም​ራት፥ የሰ​ሜኤ ልጆች፤ 22ይሰ​ጳን፥ ዖቤድ፥ ኤሊ​ኤል፤ 23ዓብ​ዶን፥ ዝክሪ፥ ሐናን፤ 24ሐና​ንያ፥ አን​በሪ፥ ኤላም፤ አና​ቶ​ትያ፥ 25ይቲን፥ ይፍ​ዴያ፥ ፋኑ​ኤል፥ የሶ​ሴቅ ልጆች፤ 26ሸም​ሸ​ራይ፥ ሸሃ​ሪያ፥ ጎቶ​ልያ፤ 27ያሬ​ሽያ፥ ኤል​ያስ፥ ዝክሪ፥ የይ​ሮ​ሐም ልጆች። 28እነ​ዚህ በት​ው​ል​ዶ​ቻ​ቸው አለ​ቆች ነበሩ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች ነበሩ፤ እነ​ዚህ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጡ።
29የገ​ባ​ዖን አባት በገ​ባ​ዖን ይኖር ነበር#አን​ዳ​ንድ የዕብ. ዘር “የገ​ባ​ዖን አባት ይኢ​ዔል” ይላል። የሚ​ስ​ቱም ስም መዓካ ነበር፤ 30የበ​ኵር ልጁ ዓብ​ዶን፥ ሱር፥ ቂስ፥ በኣል፥ ኔር፥ ናዳብ፥ 31ጌዶ​ርና፥ ወን​ድሙ ዛኪር ሜቅ​ሎት፤ 32ሜቅ​ሎ​ትም ሳም​አን ወለደ፤ እነ​ርሱ ደግሞ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ፊት ለፊት ተቀ​መጡ።
የን​ጉሥ ሳኦል ትው​ልድ
33ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦ​ልን ወለደ፤ ሳኦ​ልም ዮና​ታ​ንን፥ ሜል​ኪ​ሳን፥ አሚ​ና​ዳ​ብን፥ አስ​በ​ኣ​ልን ወለደ። 34የዮ​ና​ታ​ንም ልጅ መሪ​በ​ኣል ነበረ፤ መሪ​በ​ኣ​ልም ሚካን ወለደ። 35የሚ​ካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓ፥ አካዝ ነበሩ። 36አካ​ዝም ይሆ​ዓ​ዳን ወለደ፤ ይሆ​ዓ​ዳም ዓሌ​ሜ​ትን፥ ዓዝ​ሞ​ትን፥ ዘም​ሪን ወለደ፤ ዘም​ሪም ማሴ​ዕን ወለደ። 37ማሴ​ዕም በዓ​ናን ወለደ፤ ልጁም ራፋያ ነበረ፤ ልጁ ኤል​ዓሣ፥ ልጁ ኤሴል፤ 38ለኤ​ሴ​ልም ስድ​ስት ልጆች ነበ​ሩት፤ ስማ​ቸ​ውም ይህ ነበረ፤ ዓዝ​ሪ​ቃም፥ በኬ​ርዩ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቦኬ​ርዮ” በኵሩ ብሎ ለአ​ዘ​ረ​ቃም ይቀ​ጥ​ልና 6ኛ አሣ የሚል ይጽ​ፋል ግእዙ 5 ብቻ ይጽ​ፋል። እስ​ማ​ኤል፥ ሰዓ​ርያ፥ አብ​ድዩ፥ ሐናን፤ እነ​ዚህ ሁሉ የአ​ሴል ልጆች ነበሩ። 39የወ​ን​ድ​ሙም የአ​ሴል ልጆች፤ በኵሩ ኡላም፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ኤያስ፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ኤሊ​ፋ​ላት። 40የኡ​ላም ልጆች ጽኑ​ዓን ኀያ​ላ​ንና ቀስ​ተ​ኞች ነበሩ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም መቶ አምሳ የሚ​ያ​ህሉ ብዙ ልጆ​ችና የልጅ ልጆች ነበ​ሩ​አ​ቸው፤ እነ​ዚህ ሁሉ የብ​ን​ያም ልጆች ነበሩ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ