መጽሐፈ ጥበብ 18
18
1 #
ዘፀ. 13፥17-22። ላንተ ቅዱሳን ግን በጣም ታላቅ ብርሃን ነበር፤
የሚሰሟቸው ነገር ግን የማያያቸው ግብጻውያን
እነርሱ ሥቃይ ያልደረሰባቸው በመሆኑ ዕድለኞች ይሏቸዋል።
2በፊት ለደረሰባቸው በደል፥ የበቀል ጉዳት ባለማድረሳቸው አመሰገኗቸው።
ስላለፈው ጥላቻቸውም ይቅርታ ለመኗቸው።
3ከጨማው በተቃራኒ ለሕዝቦችህ የእሳት አምድን፥
ባልታወቀው ጉዟቸው፥ በተስፋ ስደታቸው፥
ይረዳቸው ዘንድ ለዘብ ያለ ፀሐይን ሰጠሃቸው።
4እነኛ የማይደበዝዘውን የሕግህን ብርሃን ለዓለም ይሰጡ ዘንድ
የላክኻቸውን ልጆችህን፥ በምርኮኝነት ይዘው የነበሩት ግን፥
ብርሃንን አጥተው በጨለማ መታሰር ይገባቸዋል።
ስድስተኛው ተቃርኖ፦ የሞት ምሽትና የድኀንነት ምሽት
5የቅዱሳኑ ልጆች የሆኑትን ሕፃናት ለመግደል እነርሱ እንደወሰኑ፥
ለአደጋ ከተጋለጡትም መሀል አንድ ልጅ ብቻ እንደተረፈው ሁሉ፥
አንተም ልጆቻቸውን በሙሉ ውሃው፥ ማዕበሉም እንዲያጠፋቸው አደረግህ።
6አባቶቻችን ያችን ምሽት አስቀድመው ያውቋት ነበር፤
እምነታቸውን በማን ላይ እንደጣሉ ያውቁም ስለ ነበር፥
ቃል ኪዳኑ እንደሚፈጸም እርግጠኞች ነበሩ።
7ስለዚህም ሕዝቦችህ የጻድቃኑን ደኀንነትና የጠላትን መጥፋት ይጠባበቁ ነበር።
8በተቀናቃኞቻችን ላይ ባወረድከው በቀል፥ እኛን አከበርከን፥ ወዳንተም ጠራኸን።
9ከደጋጐች የተፈጠሩ ቅዱሳን ልጆች፥ በምሥጢረ መሥዋዕት አቀረቡ፤
በስምምነት ይህን ቅዱስ ሕግ አጸደቁ፤
ቅዱሳን በጎውንና ክፉውን ይጋሩ ዘንድ ወሰኑ፤
ያኔውኑም ያባቶችን መዝሙር ዘመሩ።
10የጠላቶቻቸው ጩኸት ከያለበት አስተጋባ፤
ስለልጆቻቸው የሚያዝኑ ሰዎች ዋይታም ከሩቅ ይሰማል፤
11ጌታና አገልጋይ ተመሳሳይ ቅጣት ወረደባቸው፤
ተራው ሰውና ንጉሡም የአንድ መከራ ገፈት ጨለጡ።
12በአንድ ዓይነት ሞት በመመታታቸው ለቍጥር የሚታክቱ ሬሳዎች ነበሯቸው።
ቀሪዎቹም ሊቀብሯቸው አልቻሉም፤
የፍሬዎቻቸው አበባዎች ባንድ ጊዜ ረግፈውባቸዋልና።
13በአስማቶቻቸው ተማምነው ያላመኑት ሁሉ፥ የበኩር ልጆቻቸው በሞቱባቸው ጊዜ፥
ይህ ሕዝብ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አምነው ተቀበሉ።
14ሰላማዊ ጸጥታ በሁሉም ላይ በሰፈነ ጊዜ፥ ሌት ከተጋመሰች በኋላ፥
15ኃያሉ ቃልህ ከንጉሣዊው ዙፋን እንዳትጠፋ በተፈረደባት መሬት እምብርት ላይ እንደ ጨካኝ ጦረኛ ከሰማይ ዘሎ ወረደ።
የማያወላውለውን ትእዛዝህን እንደ ሰላ ሠይፍ ይዞ በመውረድ፥
16ዓለምን በሞት አጥለቀለቃት፤ ያረፈው በምድር ላይ ቢሆንም ሰማይን ነክቷል።
17ወዲያው ሕልሞችና አስፈሪ ቅዠቶች አሸበሯቸው፤
ያልጠበቁትም ፍርሃት አስጨነቃቸው።
18ወዲያና ወዲህ ግማሽ በድን አካላቸው ተጥሏል፤
ስለምንም አንደሚሞቱ ይናገሩ ነበር።
19ያስጨነቋቸው ሕልሞች
ይህ ቅጣት ስለምን እንደ ተፈረደባቸው ሳያውቁት እንዳያልፉ አድርጓቸዋልና።
በበረሃ ውስጥ አንዣቦ የነበረው የዕልቂት አደጋ
20 #
ዘኍ. 16፥41-50። ይሁን እንዱ የሞት ጽዋ በጻድቃኖችም ላይ ደርሷል።
ብዙዎችም በበረሃ አልቀዋል፤ ቁጣው ግን አልበረታባቸውም፤
21አንድ ንጽሕ ሰው ከመዓቱ አድኗቸዋልና።
የተቀደሱ መሣሪያዎቹን፥ ጸሎቱንና የስርየት ዕጣን በመያዝ ቁጣውን ተጋፈጠው፤
አገልጋይህ መሆኑንም በማስመስከር መዓቱን አስወገደ።
22ጥላቻን አስወገደ፤ በጉልበት አልነበረም፥ በመሣሪያም አልነበረም፥
ለአባቶች ያደረገውን መሐላ፥ የገባውንም ቃል ኪዳን በማስታወስ
ቀጪውን ስለ ተስፋው ቃል በመለመን ነበር እንጂ።
23ቁጣን ባቆመውና ወደ ሕያዋንም እንዳይጠጋ ባገደው ጊዜ፥
አስክሬኖች ተከምረው ነበር።
24መላው ዓለም በቀሚሱ ላይ ተስሎ ነበር፤
የከበሩ የአባቶች ስሞች በአራቱ ረድፍ ደንጊያዎች፥
ያንተ ግርማም በአክሊሉ ላይ ተቀርጿል።
25ደምሳሹም ከእነኚህ ራቀ፤ ፈራቸውም፤
ይሄው ቁጣም በቂ ነበር።
Currently Selected:
መጽሐፈ ጥበብ 18: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ