መጽሐፈ ጥበብ 19

19
ሰባተኛው ተቃርኖ፦ ቀይ ባሕር
1በክፉዎች ላይ ግን እስክ መጨረሻው ምሕረት የለሹ ቁጣ ሠርቶባቸዋል፤ ቀድሞውኑም ምን እንደሚሠሩ እራሱ ያውቅ ነበር፤
2ሕዝቡን ካሰናበቱና በፍጥነትም እንዲወጡ ካደረጉ በኋላ
እንደምን ሐሳባቸውን ቀይረው እንደሚያሳድዳቸውም እራሱ ያውቅ ነበርና።
3በኀዘን ላይ ሳሉ፥ በሞቱባቸው ዘመዶቻቸው መቃብር ላይ
በመሪር ኀዘን ያለቅሱ በነበሩበት ጊዜ፥
ሌላ የእብደት ሐሳብ ብልጭ አለባቸው፤
ያባረሯቸውንና እንዲወጡ የለመኗቸውን ሰዎችም እንደ ኮብላዮች ያሳድዷቸው ጀመር።
4ዋጋቸው የሆነው ዕጣቸውም እንዲህማወደ ከፋው ድርጊት ገፋፋቸው፤
ከዚህ ቀደም የሆነውንም ሁሉ ረሱ።
በመከራ ላይ መከራን ይጨምሩ ዘንድ፥ ቀሪውን ከፍተኛም ቅጣት ይቀበሉ ዘንድ ይህን ፈጸሙ።
5ሕዝቦችህ ግን ፈጽሞ ያልታሰበ ጉዞ አደረጉ፤
በዚያም እጅግ ያልተጠበቀ ሞትም አጋጠማቸው።
6ልጆችህ ከመጐዳት ይድኑ ዘንድ፥
ፍጥረታታ በሙሉ ትእዛዞችህን በማክበር ሁለመናቸውን ለወጡ።
7ደመና በሠፈራቸው ላይ አጠላ፤ ውሃ በነበረበት ደረቅ መሬት ብቅ አለ፤
ቀይ ባሕር መሰናክል የሌለበት መንገድ፥ ሞገደኛውም ማዕበል የለመለመ መስክ ሆነ።
8ሕዝቡ በእጅህ ከለላ ስር ሆኖ፥
በድንቅ ሥራዎችህ እየተደመመ ባሕሩን አቋረጠ።
9እነርሱ ለግጦሽ በመስክ እንደተሰማሩ ፈረሶች ሆኑ፤
እንደ በግ ግልገሎቾ ዘለሉ፤ ጌታ ሆይ አንተን አዳኛቸውንም እየዘመሩ ያመሰግኑህ ነበር።
10በዚያን ጊዜ፥ የስደት ጉዟቸውን አስታውሱ፤
መሬት በእንስሳት ፈንታ ትንኞችን አፈራች፤
ወንዙም በአሳዎች ምትክ እልፍ አዕላፍ ዕንቁራሪቶችን ተፋ።
11ቆየት ብለውም፥ ወፎች ህልውናቸውን በአዲስ መንገድ ሲያገኙ ተመለከቱ፤
የምግብ አምሮታቸው በተቀሰቀሰ ጊዜም ጣፋጭ ምግብን ለመኑ፤
12እነርሱንም ለማጥገብ፥ ድርጭቶች ከባሕር ውስጥ ወጡ።
ግብጽ ከሶዶም የበለጠ ወንጀለኛ ነች
13ከአሸባሪው ነጐድጓዳዊ ማስጠንቀቂያ በኋላ፥ ቅጣቱ በኃጢአተኞቹ ላይ ዘነበ።
በመጻተኞች ላይ ላሳዩትም ጥላቻ የወንጀሎቻቸውን ዋጋ አገኙ።
14ሌሎቹም ቢሆኑ ባዕዳኑን በጥሩ ሁኔታ አላስተናገዱም፤
ግብጻውያኑ ግን እንግዳዎቻቸውንና ባለውለታዎቻቸውን ባሮች አደረጉ።
15በበለጠ ደግሞ ኃጢአተኞቺ ይቀጡበታል፤
ባዕዳኑን ከጥላቻ የተነሣ በሚገባ አላስተናገዷቸውም።
16የኋላኞቹ ግን እንደ እነርሱ መብት ያላቸውን ሰዎች
በደመቀ ሥነ ሥርዓት ከተቀበሏቸው በኋላ፥ እጅግ አድካሚ ሥራዎችን ሰጧቸው።
17በጻድቁ በር ላይ እንደነበሩት ኃጢአተኞች፥ እነርሱም ታወሩ፤
ጨለማ ሊውጣቸው በዙሪያቸው ባሰፈሰፈ ጊዜም፥
በበሩ ለመውጣት እያንዳንዱ መንገድን በዳሰሳ ማግኘት ነበረበት።
አዲስ ስምምነት በተፈጥሮ ውስጥ
18የበገና ዜማ ቃናው ሳይለወጥ የድምፁ አወራረድ ሊለዋወጥ እንደሚችል፥
የተፈጥሮም አካላት እንዲሁ በአዲስ ተቀናጁ፤ የሆነውም ሁሉ እንዲህ ነበር፥
19በመሬት የሚኖሩት እንስሳት፥ በውሃ ውስጥ እየዋኙ ይኖሩ የነበሩ ደግሞ፥
በመሬት ላይ ይኖሩ ጀመር፤
20እሳት በውሃ ውስጥ ኃይሉን ጨመረ፤ ውሃም እርሱን የማጥፋት ኃይሉን ዘነጋ፤
21የእሳት ነበልባሎች ደግሞ፥ በውስጣቸው ዘለው የሚገቡትን ትናንሽ እንስሳት ሥጋ መለብለብ አቃታቸው፤
በረዶ የሚመስለውንና በቀላሉ የሚቀልጠውንም ሰማያዊ ምግብ ሊያሟሙት አልቻሉም።
መደምደሚያ
22ጌታዬ ሆይ በእርግጥም ሕዝብህን በሁሉም ነገር ከፍ አድርገሃል፤ አክብረሃልም፤
በየትኛውም ጊዜና ሥፍራ እርዳታህን አልነፈግኻቸውም።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ