መጽሐፈ ሲራክ 8
8
ብልህነትና የተፈጥሮ ዕውቀት
1ችሎታ ላለው ከትልቅ ሰው አትከራከር፤ አለበለዚያ በእጁ ትወድቃለህ። 2ከሀብታም ሰው ጋር አትጋጭ አለበለዚያ ይጫንኻል፤ ምክንያቱም ወርቅ ብዙዎችን አጥፍቷል። የነገሥታትንም ልቦና መንገድ አስቷል። 3ከተሟጋች ጋር አትከራከር፤ በእሳቱ ላይ እንጨት አትከምር። 4አያቶችህን እንዳይሰደቡብህ ከነውረኛ ሰው ጋር አትዘባበት። 5በኃጢአቱ የሚጸጸተውን ሰው አትውቀሰው፤ ሁላችንም በደለኞች መሆናችንን አስብ። 6ሽማግሌን አትጥላ፥ ከኛም አንዳንዶቻችን እየሸመገልን ነውና። 7በሌላው ሞት አትደሰት፥ ሁላችንም ሟቾች መሆናችንን አትዘንጋ።
ባህል
8የጥበበኞችን ንግግር አታቃል፤ ምሳሌዎቻቸውን ተከተል፤ ታላላቆችን የማገልገል እውቀትና ጥበብ ከእነርሱ ትማራለህና። 9ሽማግሌዎች የሚናገሩትን አታቀል፥ እርሱም የተማሩት ከአባቶቻቸው ነውና፤ ብልህነትንና በአስፈላጊውም ጊዜ መልስ የመስጠት ጥበብን የምትማረው ከነሱ ነው።
ማስተዋል
10በነበልባሉም ትቃጠላለህና የኃጢአተኛን ከሰል አታቀጣጥል። 11ለተሳዳቢ አትበገር፥ በቃልህ ሊያጠምድህ ይችላል። 12ከአንተ ለሚያይል አታበድር፤ ካበደርክም እንደጠፋብህ ቁጠረው። 13ከችሎታህ በላይ ዋስ አትሁን፥ ከተዋስክ ለመክፈል ተዘጋጅ። 14ከዳኛ ጋር አትካሰስ፥ ምክንያቱም ለእርሱ ይፈረድለታል። 15ከችኩል ሰው ጋር አትጓዝ፥ አለበለዚያ ሸክም ይሆንብሃልና፤ እሱ በገዛ ፈቃዱ የሚመራ ነው፤ በእርሱም ጥፋት ሁለታችሁም አብራችሁ ትጠፋላችሁ። 16ከቁጡ ሰው ጋር አትከራከር፤ ሰዎች በሌሉበት ከሱ ጋር አትሂድ፥ ደም መፍሰስ ለእርሱ ምኑም አይደለምና፤ ሰው በሌለበት ሊጎዳህ ይችላል። 17ከሞኝ ምክር አትጠይቅ፥ ምስጢር መቋጠር አይችልምና። 18ምን እንዲሆን አታውቅምና በእንግዳ ፊት ምሥጢር አታውጣ። እንግዳው እንዴት ሊጠቀምበት እንደሚችል አታውቅምና። 19ለማንም ልብህን አትግለጥ፤ መልካም ተግባሮቻቸውም ላይ አትተማመን።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 8: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ