መጽሐፈ ሲራክ 9

9
ሴቶች
1 # ዘኍ. 5፥12-15። በምትወዳት ሚስትህ ላይ አትቅና፤ እንዴት እንደምትጎዳህ አታስተምራት፤ 2እራስህን በሴት እጅ አትጣል። ካልሆነ ግን በቁጥጥር ሥር ትወድቃለህ። 3ከሴተኛ አዳሪ ጋር አተዋዋል፥ በወጥመዷ ልትወድቅ ትችላለህና። 4አንተ በተንኮል ሥራዋ እንዳትጠመድ፥ አዝማሪት ሴትን አታዘውትር። 5ውብ ኮረዳን አትመልከት፤ ምናልባት አንተ እና እርሷ አንድ ዓይነት ቅጣት በራሳችሁ ላይ ታመጡ ይሆናል። 6ለጋለሞታዎች ልብህን አትስጥ፤ ካልሆነ ግን ርስትህን ታጣለህ። 7በከተማ መንገዶች ዙሪያ፥ ዐይኖችህ አያማትሩ። ጭር ወዳለው ቦታም አትሂድ። 8ከቆንጆ ሴት ዓይንህን መልስ፤ የሌላ የሆነውን ውበት አትከጅል። በሴት ቁንጅና ምክንያት ብዙዎች ተሳስተዋል፤ ይህም ስሜትን እንደ እሳት ያቀጣጥላል። 9ባል ካላት ሴት ዓይንህን መልስ፤ ከሷ ጋር አብረህ ወይን ጠጅ አትጠጣ፤ ልብህም ወደ እርሷ ከተሳበ፥ ራስህን መግታት አቅቶህ ችግር ላይ ትወድቃለህ።
ከሰዎች ጋርስ ለሚኖርህ ግንኙነት
10የቀድሞ ወዳጅህን አትተው፤ አዲስ ወዳጅህ እሱን አይተካከለውም፤ አዲስ ወዳጅ እንደ አዲስ ወይን ጠጅ ነው፤ ሲያረጅ ደስ እያለህ ትጠጣዋለህ። 11በኃጢአተኛ መልካም ዕድል አትቅና፤ ምን ዓይነት አሳዛኝ ፍጻሜ እንደሚጠብቀው አታውቅምና። 12ክፉዎችን ደስ የሚያሰኛቸው አንተን አያስደስትህም፤ ከመሞታቸው በፊተ በዚህ ዓለም ሳይቀጡ እንደማይቀሩ አስታውስ። 13ለመግደል ችሎታ ካለው ሰው ራቅ፤ የሞት ፍርሃት አያድርብህም። ግን ወደሱ ስትቀርብ በጣም ተጠንቀቅ፤ ሊገድልህ ይችላል፤ በወጥመድ መካከል የምትሄድና በከተማይቱ ምሽግ ላይ የምትራመድ መሆንህን አትዘንጋ። 14በተቻለህ መጠን ጓደኛህን አትተው፤ ከጥበበኞች ጋር ተማከር። 15ዕውቀት ካላቸው ሰዎች ጋር ተነጋገር፤ ንግግሮችህ ሁሉ ስለ ልዑል እግዚአብሔር ሕግ ይሁን። 16ጻድቃኖች ካንተ ጋር የሚመግገቡ ጓደኞችህ ይሁኑ፤ ኩራትህ እግዚአብሔርን በመፍራት ይሁን። 17ብልሃተኛ በእጁ ሥራ ይመሰገናል፥ የሕዝብ አለቃ በቃሉ ጥበብ ይመሰገናል፤ 18ለፋላፊ ሰው ለከተማው ሽብር ነው። ልቅ ተናጋሪም አይወደድም።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ