መጽሐፈ ሲራክ 5

5
ሀብትና አጉል ድፍረት
1በሀብትህ አትመካ፤ ሀብቴ ይበቃኛል አትበል፤ 2የልብህን ፈቃድ ለመፈጸም በስሜትህ ና በጉልበትህ አትመራ። 3እግዚአብሔር በርግጥ ይቀጣሃልና፥ “በኔ ላይ ሥልጣን የሚኖረው ማነው?” አትበል። 4#መክ. 8፥11።እግዚአብሔር ትዕግሥት ትልቅ ነውና፥ “ኃጢአት ሠራሁ ምን መጣብኝ?” አትበል። 5በበደል ላይ በደል እየከመርህ፥ ይቅርታ አገኛለሁ ብለህ እርግጠኛ አትሁን። 6“ኀዘኔታው ታላቅ ነው፤ ኃጢአቶቼንም ይቅር ይልልኛል” አትበል። 7ሳትዘገይ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ፤ ነገ ከነገ ወዲያ እያልህ ቀኑን አታራዝም፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቁጣ በድንገት ከተፍ ይላል፤ በቅጣት ቀን ትደመሰሳለህ። 8አላግባብ በተገኘ ሀብት አትመካ፤ በመከራ ቀን ለምንም አያገለግልህም።
ግልጽነትና ራስን መሆን
9በመጣው ነፋስ ሁሉ አትነፈስ፤ ባገኘኸው መንገድ ሁሉ አትሂድ። በሁለት ምላስ እንደሚናገረው ኃጢአተኛ አትሁን 10በእምነትህ ጽና፤ በቃልህ ታመን፤ 11ለመስማት የፈጠንክ፥ ለመልስ የገዘገየህ ሁን። 12ጉዳዩ ከገባህ ለጐረቤትህ መልስለት፤ አለበለዚያ እጅህን በአፍህ ላይ አድርግ። 13ክብርም፥ ውርደትም ከንግግር ይገኛል፤
ምላስ የባለቤቷን ውድቀት ታስከትላለች።
14የሐሜተኛ ዝነኝነት ይቅርብህ፤ በምላስህ የሐሜት ወጥመድ አትዘርጋ፤ በሌላ ላይ እፍረት እንደሚወድቅበት፤ በአታላይ ሰው ላይም ብርቱ ፍርድ ይወድቅበታል። 15ከታናናሾችም ሆነ ከታላላቆች፤ ስሕተቶች ተጠንቀቅ፤

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ