መጽሐፈ ሲራክ 47
47
ናታን
1 #
2ሳሙ. 7፥2፤3፤ 12፥1። ከእርሱም በኋላ በዳዊት ዘመን ትንቢት ለመናገር ናታን ተነሣ። ዳዊት 2#1ሳሙ. 17፥34—18፥7፤ 2ሳሙ. 5፥7፤ 8፥1፤ 12፥13።በኀብረት መሥዋዕት ላይ ስብ እንደሚለይ፥ ዳዊትም ከእስራኤላውያን መካከል እንዲሁ ተመረጠ። 3ከግልገሎቹ እንደሚጫወት ከአንበሶች ጋር፥ ከጠቦቶች እንደሚጫወት ከድቦች ጋር ተጫወተ። 4በልጅነቱስ ቢሆን ድንጋይ በመወንጭፍ ወርውሮ፥ ጉረኛው ጐልያድን ዘርሮ፥ ግዙፉን ሰው ጥሎ፥ የሕዝቡን እፍረት አልገፈፈምን? 5ታላቁንና ኃያሉን ልዑል እግዚአብሔርን ለመነ፥ እርሱም ለቀኝ እጁ ብርታትን ሰጠው፥ የማይበገረውንም ጦረኛ በመግደል የወገኖቹን ብርታት ዳዊት አረጋገጠ። 6ስለዚህም የዐሥር ሺህ ሰው ክብር ተሰጠው፥ ጌታን ባመሰገኑም ጊዜ፥ አሞገሱት የክብርም አክሊል ደፉለት። 7በየግምባሩ ጠላቶቹን ደምስሷል፥ ፍልስጥኤማውያን ተቃዋሚዎቹን አጥፋቷል፤ ኃያልነታቸውንም ለምን ጊዜም አብስሯል። 8በሥራዎቹ ሁሉ፥ ቅዱሱንና ኃያሉን እግዚአብሔርን ያመሰግናል። ለፈጣሪውም ባለው ጽኑ ፍቅር መንፈሱን ሁሉ በመዝሙሮቹ ላይ አሳረፈ። 9በመሠዊያው ፊት መዘምራንን አቆመ፥ ጣዕመ ዜማቸውንም እንዲያሰሙ አደረገ። 10ታላላቅ ግብሮችን አዘጋጀ፥ በዓላቱን በድምቀት አከበረ፥ የእግዚዘአብሔርን ቅዱስ ስም አመሰገነ፥ ቤተ መቅደሱም ከማለዳ አንስቶ በምስጋና ተሞላ። 11ጌታ ኃጢአቱን ይቅር አለው፥ ከመቼውም በበለጠ ብርታትን ሰጠው፥ የንጉሥ ቃል ኪዳን ገባለት፥ በእስራኤልም ታላቅ ዙፋን ሰጠው።
ሰሎሞን
12በእርሱ ምክንያት ሕይወቱን በተድላ ያሳለፈው ጥበበኛው ልጁ ዙፉኑን ወረሰ። 13#1ነገ. 4፥21-32።ሰሎሞን በነገሠበት ዘመን ሰላም ሰፈነ፥ በዙሪያውም ሁሉ እግዚአብሔር ሰላምን ሰጠው፥ ለስሙ መጠሪያ የሚሆን ቤት፥ ዘላለማዊ ቤተ መቅደሱንም ይሠራ ዘንድ አጨው። 14ለጋ ወጣት ብትሆንም፥ እንደ ወንዝ በእውቀት የተሞላህ ጥበበኛ ነበርህ፥ 15መንፈስህ ምድርን ዳሰሳት፥ በምሥጢራዊ ዘይቤዎችህም ሞላሃት፥ 16ዝናህ እሩቅ በተባሉት ደሴቶች ላይ እንኳ ናኝቷል፥ ስለ ሰላምህም የተወደድህ ነበርህ። 17መዝሙሮችህ፥ ምሳሌዎችህ፥ ዘይቤዎችህ፥ መልሶችህም በዓለም ዙሪያ አድናቆትን አትርፈዋል። 18#1ነገ. 10፥21፤27።በጌታ በእግዚአብሔር፥ የእስራኤል አምላክ በሆነው በእርሱ ስም፥ ወርቅ እንደ ቆርቆሮ ብርም እንደ እርሳስ ሰበሰብህ። 19#1ነገ. 11፥1።ሥጋህን ለሴቶች ሰጠህ፥ የፍላጐትህም ተገዥ ሆነህ፥ 20ክብርህን አሳደፍህ፥ ዘርህን አረከስና፥ በልጆችህ ላይ ቅጣትን አመጣህ፥ በዕብደትህም መከራ ወረደባቸው። 21#1ነገ. 12፥15-20።መንግሥትህ ከሁለት ተከፈለ፥ ከኤፍሬምም ዓመፀኛ መንግሥት ተነሣ። 22#2ሳሙ. 7፥15።ጌታ ግን መሐሪ ነው፥ ቃሉን አያጥፍም፥ ለመረጠው ዘር አይነሣም፥ የወደደውንም ሰው ዘር አያጠፋም። እነሆ ለያዕቆብ ምትክ ተወለት፥ ለዳዊትም ከእርሱ የሚወጣ ሥር ሰጠው።
ሮብዓም
23 #
1ነገ. 11፥43፤ 12፥10-30፤ 2ነገ. 17፥6፤18። ሰሎሞን ከአባቶቹ ጐን አረፈ፥ ዙፋኑን ለልጆቹ አንዱ፥ ከሕዝቡ መካከል እጅግ የማይረባው፥ ማስተዋል የጐደለውና ሕዝቡንም ለዓመፅ የገፋፋው ሮብዓም ወረሰ። 24የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤልን አሳሳተ፥ ኤፍሬምንም በክፋት መንገድ መራው፤ ከዚያም ወዲህ ኃጢአታቸው እጅግ በረከተ፤ ከሀገራቸውም እስኪወጡ አደረሳቸው፤ 25ፍዳው እስከመጣባቸውም ጊዜ ድረስ፥ ያልፈጸሙት ኃጢአት አልነበረምና።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 47: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ