መጽሐፈ ሲራክ 17
17
1 #
ዘፍ. 1፥26-28፤ 2፥7። ጌታ ሰውን ከመሬት ፈጠረ፤ ወደ እርሷም ይመልሰዋል። 2ለሰዎች ብዙ ቀናትንና ጊዜም ሰጣቸው፤ በምድርም በሚገኘው ላይ ሁሉ ሥልጣንን ሰጣቸው። 3እንደ ራሱ ብርታትን አለበሳቸው፤ በአምሳሉ ፈጠራቸው። 4የዱር አውሬዎችና ወፎች እንዲታዘዟቸው፥ የምድር ፍጥረት ሁሉ እንዲፈራቸው አደረገ።#17፥4 5. ከጌታ የአምስት ኃይላት አጠቃቀም ተቀብለዋል፤ እንደ ስድስተኛ የተሰጣቸውም የብልህነት ድርሻ፥ ሰባተኛውም የኃይሉን የሚገልጽ ነው። 6ምላስን፥ ዓይንና ጆሮን ሠራላቸው፤ የሚያስቡበትንም ልቦና ሰጣቸው። 7#ዘፍ. 2፥17።በዕውቀትና በማስተዋል ሞላቸው፤ ደግንና ክፉን እንዲለዩ አደረጋቸው። 8የሥራዋቹንም ታላቅነት እንዲያዩ፥ በልባቸውም የራሱን ብርሃን አኖረ። 9ስለ ድንቅ ሥራዎቹ እንዲገሩ፥ 10ቅዱሱን ስሙን እንዲያመሰግኑ፥ 11ዕውቀትንም በፊታቸው አኖረ፥ የሕይወትንም ሕግ ሰጥቷቸዋል። 12ከነሱ ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን ገብቷል፤ ፍርዶቹንም ገልጾላቸዋል። 13ዐይኖቻቸው የክብሩን ታላቅነት አይተዋል፤ ጆዎቻቸው የድምፁን ግርማ ሰምተዋል። 14“ከክፉ ሁሉ ተጠንቀቁ” አላቸው፥ እያንዳንዳቸው ባልንጀሮቻቸውን በተመለከተም ትዕዛዝ ሰጥቷቸዋል።
መለኮታዊው ዳኛ
15መንገዶቻቸው ከእይታው አያመልጡም፤ በዐይኑም ይከታተላቸዋል።#17፥15 16. ከልጅነታቸው ጀምሮ መንገዶቻቸው ወደ ክፋት የሚመሩ ስለ ሆኑ ያን ድንጋይ የሆነ ልብ ወደ ሥጋ ልብ ሊቀይሩት አይችሉም። 17በእያንዳንዱ ሀገር አስቀምጧል፥ ይሁን እንጂ እስራኤል የእግዚአብሔር ድርሻ ናት።#17፥17 18. እስራኤል የበኩር ልጁ እንደመሆኑ መጠን በጥንቃቄ ይንከባከበዋል፤ የፍቅሩን ብርሀን ያለአንዳች መዘንጋት ያጋራዋል። 19ሥራዎቻቸው ሁሉ በሱ ፊት እንደ ፀሐይ ግልጽ ናቸው፤ ዐይኖቹ ሁልጊዜ በባሕሪያቸው ላይ ያነጣጥራሉ። 20ክፋታቸው ከእርሱ አይሰወርም፤ ኃጢአቶቻቸውም በፊቱ ይቀርባሉ። #17፥20 21. ነገር ግን ጌታ መልካም በመሆኑና እንዴት እንደ ተፈጠሩ በማወቁ፥ አይተዋቸውም፤ እነሱንም ከማረም አይቆጠብም። 22ምጽዋት ለእርሱ እንደ ቀለበት ማኀተም ነው፤ በሰው ውስጥ ያለው ደግነት ለልክ እንደ ዐይን ብሌን ያስደስተዋል፤ 23አንድ ቀን ተነሥቶ ይሸልማቸዋል፤ ዋጋቸውን ለየራሳቸው ይከፍላቸዋል። 24ነገር ግን ንስሐ ለሚገቡ እንዲመለሱ ይፈቀድላቸዋል፤ ተስፋ የቆረጡትንም ያበረታቸዋል።
የንስሐ ጥሪ
25 #
ኤር. 3፥12። ወደ እግዚአብሔር ተመለስ፥ ኃጢአቶችህንም አውግዝ፥ በፊቱ ለምን፥ እሱንም አታስቀይመው። 26ወደ ልዑል እግዚአብሔር ተመለስ፤ ከክፉ ነገር ራቅ፤ መጥፎውን ሁሉ ጥላ። 27#መዝ. 6፥5፤ ኢሳ. 38፥18፤ ባሮክ 2፥17፤18።በሕይወት እያለን ከፍ ከፍ ካላደረግነው፥ ሲኦል ወርዶ የሚያመሰግነው ይኖራልን? 28የሞቱትን እንደ ሌሎች ሁሉ ማመስገን አይችሉም፤ እግዚአብሔርን የሚያወድሱ ሕያዋንና ጤነኞች ብቻ ናቸው። 29የእግዚአብሔር ምሕረት ምንኛ ታላቅ ነው፤ ወደሱ ለሚመለሱ ሰዎች ይቅርታው ምንኛ የበዛ ነው። 30የምንሻው ሁሉ ሊኖረን አይችልም፤ ሰዎች ዘላለማዊ አይደለንምና። 31ከፀሐይ የበለጠ ድምቀት ያለው አለን? እንዲያም ሆኖ ግን ይደበዝዛል፥ ሥጋና ደምም ከክፋት በስተቀር የሚያልሙት የለም። 32አምላክ የሰማይ ሠራዊትን ይቆጣጠራል፥ እኛ ግን ትቢያና አመድ ብቻ ነን።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 17: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ