መዝሙረ ዳዊት 105:39-45
መዝሙረ ዳዊት 105:39-45 መቅካእኤ
ደመናን ለመሸፈኛ ዘረጋባቸው፥ እሳትንም በሌሊት እንዲያበራላቸው። ለመኑ፥ ድርጭትንም አመጣላቸው፥ የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው። ዓለቱን ሰነጠቀ፥ ውኃውም ፈለቀ፥ ወንዞች በበረሃ ፈሰሱ፥ ለአገልጋዩ ለአብርሃም የነገረውን ቅዱስ ቃሉን አስታውሶአልና። ሕዝቡንም በደስታ የተመረጡትንም በእልልታ አወጣ። የአሕዛብንም አገሮች ሰጣቸው፥ ከሕዝቦችም ድካም ወረሱ፥ ሕጉን ይጠብቁ ዘንድ፥ ሥርዓቱንም ይፈልጉ ዘንድ። ሃሌ ሉያ።

