መጽሐፈ መዝሙር 105:39-45

መጽሐፈ መዝሙር 105:39-45 አማ05

በሚሄዱበትም ጊዜ በደመና ጋረዳቸው፤ በሌሊትም፥ ብርሃን የሚሰጣቸውን እሳት አዘጋጀላቸው። ምግብ በጠየቁት ጊዜ ድርጭቶችን ላከላቸው። ከሰማይ እንጀራን ልኮ አጠገባቸው። አለቱን ሰነጠቀ፤ ውሃም ወጣ፤ በበረሓውም ውስጥ እንደ ወንዝ ውሃ ፈሰሰ። ለአገልጋዩ ለአብርሃም የሰጠውን ቅዱስ ቃል ኪዳን አሰበ። ስለዚህ የተመረጠውን ሕዝቡን መርቶ አወጣ፤ እነርሱም በደስታ ዘመሩ፤ እልልም አሉ። የሌሎች ሕዝቦችን ምድር ሰጣቸው፤ ሌሎች የደከሙባቸውንም እርሻዎች አወረሳቸው። ይህንንም ሁሉ ማድረጉ ሕዝቡ ድንጋጌውን እንዲጠብቁና ሕጉንም እንዲፈጽሙ ነው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}