መዝሙር 105:39-45
መዝሙር 105:39-45 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በሥራቸውም ረከሰች፥ በጣዖታቸውም አመነዘሩ። እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ቍጣን ተቈጣ፥ ርስቱንም ተጸየፈ። በጠላቶቻቸውም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። የሚጠሉአቸውም ገዙአቸው። ጠላቶቻቸውም አሠቃዩአቸው፥ ከእጃቸውም በታች ተዋረዱ። ብዙ ጊዜ አዳናቸው፤ እነርሱ ግን በምክራቸው አስመረሩት፥ በኀጢአታቸውም መከራ ተቀበሉ። እንደ ተጨነቁም ተመለከታቸው፥ ጸሎታቸውንም ሰማቸው፤ ለእነርሱም ኪዳኑን አሰበ፥ እንደ ምሕረቱም ብዛት አዘነላቸው።
መዝሙር 105:39-45 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ደመናን እንደ መጋረጃ ዘረጋላቸው፤ እሳትም በሌሊት አበራላቸው። በለመኑትም ጊዜ፣ ድርጭት አመጣላቸው፤ የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው። ዐለቱን ሰነጠቀ፤ ውሃም ተንዶለደለ፤ እንደ ወንዝም በበረሓ ፈሰሰ። ለባሪያው ለአብርሃም የሰጠውን፣ ቅዱስ የተስፋ ቃሉን አስቧልና። ሕዝቡን በደስታ፣ ምርጦቹንም በእልልታ አወጣቸው። የሌሎችን ሕዝቦች ምድር ሰጣቸው፤ የእነዚህንም የድካም ፍሬ ወረሱ፤ ይህም ሥርዐቱን ይጠብቁ ዘንድ፣ ሕጉንም ይፈጽሙ ዘንድ ነው።
መዝሙር 105:39-45 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በሚሄዱበትም ጊዜ በደመና ጋረዳቸው፤ በሌሊትም፥ ብርሃን የሚሰጣቸውን እሳት አዘጋጀላቸው። ምግብ በጠየቁት ጊዜ ድርጭቶችን ላከላቸው። ከሰማይ እንጀራን ልኮ አጠገባቸው። አለቱን ሰነጠቀ፤ ውሃም ወጣ፤ በበረሓውም ውስጥ እንደ ወንዝ ውሃ ፈሰሰ። ለአገልጋዩ ለአብርሃም የሰጠውን ቅዱስ ቃል ኪዳን አሰበ። ስለዚህ የተመረጠውን ሕዝቡን መርቶ አወጣ፤ እነርሱም በደስታ ዘመሩ፤ እልልም አሉ። የሌሎች ሕዝቦችን ምድር ሰጣቸው፤ ሌሎች የደከሙባቸውንም እርሻዎች አወረሳቸው። ይህንንም ሁሉ ማድረጉ ሕዝቡ ድንጋጌውን እንዲጠብቁና ሕጉንም እንዲፈጽሙ ነው።
መዝሙር 105:39-45 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ደመናን ለመሸፈኛ ዘረጋባቸው፥ እሳትንም በሌሊት እንዲያበራላቸው። ለመኑ፥ ድርጭትንም አመጣላቸው፥ የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው። ዓለቱን ሰነጠቀ፥ ውኃውም ፈለቀ፥ ወንዞች በበረሃ ፈሰሱ፥ ለአገልጋዩ ለአብርሃም የነገረውን ቅዱስ ቃሉን አስታውሶአልና። ሕዝቡንም በደስታ የተመረጡትንም በእልልታ አወጣ። የአሕዛብንም አገሮች ሰጣቸው፥ ከሕዝቦችም ድካም ወረሱ፥ ሕጉን ይጠብቁ ዘንድ፥ ሥርዓቱንም ይፈልጉ ዘንድ። ሃሌ ሉያ።