ኦሪት ዘኍልቊ 6:1-8

ኦሪት ዘኍልቊ 6:1-8 መቅካእኤ

ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ለእነርሱ ተናገር፦ ወንድ ወይም ሴት ራሳቸውን ለጌታ ለመለየት የናዝራዊነት ስእለት ቢሳሉ፥ ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን ይለይ፤ ከወይን ወይም ከሚያሰክር መጠጥ የሚሠራን ሆምጣጤ አይጠጣ፥ ማንኛውንም ዓይነት የወይን ዘለላ ጭማቂ አይጠጣ፤ የወይን ዘለላ ወይም ዘቢብ አይብላ። ራሱን በለየበት ወራት ሁሉ ከወይን ጠጅ የሚሠራውን ሌላ ነገር ሁሉ እንዲሁም የውስጡን ፍሬ ወይም ግልፋፊውን እንኳ አይብላ። “ራሱን ለመለየት ስእለት ባደረገበት ወራት ሁሉ በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ ለጌታ የተለየበት ወራት እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰ ይሆናል፥ የራሱንም ጠጉር ያሳድግ። “ለጌታ ራሱን በለየበት ወራት ሁሉ ወደ ሬሳ አይቅረብ። ለአምላኩ ያደረገው ቅድስና በራሱ ላይ ነውና አባቱ ወይም እናቱ ወይም ወንድሙ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ራሱን ስለ እነርሱ አያርክስ። ራሱን በለየበት ወራት ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ነው።