ዘኍልቍ 6:1-8
ዘኍልቍ 6:1-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ወንድ ወይም ሴት ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ያደርግ ዘንድ ልዩ ስእለት ቢሳል፥ ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን የተለየ ያድርግ፤ ከወይን ወይም ከሌላ ከሚያሰክር ነገር የሚገኘውን ሆምጣጤ አይጠጣ፤ የወይንም ጭማቂ አይጠጣ፤ የወይንም እሸት ወይም ዘቢብ አይብላ። ራሱን የተለየ ባደረገበት ወራት ሁሉ ከወይን የሆነውን ነገር ሁሉ ከውስጡ ፍሬ ጀምሮ እስከ ደረቀው ዘቢብ ድረስ አይብላ። “ራሱን ለመለየት ስእለት ባደረገበት ወራት ሁሉ ራሱን አይላጭ፤ ለእግዚአብሔር የተለየበት ወራት እስኪፈጸም ድረስ ቅዱስ ይሆናል፤ የራሱንም ጠጕር ያሳድጋል። “ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ባደረገበት ወራት ሁሉ ወደ ሬሳ አይቅረብ። ለአምላኩ ያደረገው ብፅዐት በራሱ ላይ ነውና አባቱ፥ ወይም እናቱ፥ ወይም ወንድሙ፥ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ሰውነቱን አያርክስባቸው። በብፅዐቱ ወራት ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነውና።
ዘኍልቍ 6:1-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፣ ‘ወንድም ሆነ ሴት ናዝራዊ ይሆን ዘንድ ራሱን ለእግዚአብሔር ለመለየት ስእለት ቢሳል፣ ከወይን ጠጅና ከሌላም ከሚያሰክር መጠጥ ይታቀብ፤ የወይንም ሆነ የሚያሰክር የሌላ መጠጥ ሖምጣጤ አይጠጣ፤ እንዲሁም የወይን ጭማቂ አይጠጣ፤ የወይን ፍሬም ሆነ ዘቢብ አይብላ። በናዝራዊነቱ ወቅት ከወይን ተክል የሚገኘውን ማንኛውም ነገር፣ የወይኑን ዘር፣ ግልፋፊውንም እንኳ ቢሆን አይብላ። “ ‘ስእለት ተስሎ ራሱን በለየበት ጊዜ ሁሉ ምላጭ ራሱን አይንካው፤ ለእግዚአብሔር የተለየበት ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ የተቀደሰ ይሁን፤ የራስ ጠጕሩንም ያሳድግ። ራሱን ለእግዚአብሔር በለየበት ጊዜ ሁሉ ወደ ሬሳ አይቅረብ። ራሱን ለእግዚአብሔር የለየበት ምልክት በራሱ ላይ ስላለ አባቱም ይሁን እናቱ፣ ወንድሙም ይሁን እኅቱ ቢሞቱ ለእነርሱ ሲል እንኳ ራሱን አያርክስ። ራሱን በለየበት ጊዜ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።
ዘኍልቍ 6:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፦ ሰው ወይም ሴት ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ያደርግ ዘንድ የናዝራዊነት ስእለት ቢሳል፥ ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን የተለየ ያድርግ፤ ከወይን ወይም ከሌላ ነገር የሚገኘውን ሆምጣጤ አይጠጣ፥ የወይንም ጭማቂ አይጠጣ፤ የወይን እሸት ወይም ዘቢብ አይብላ። ራሱን የተለየ ባደረገበት ወራት ሁሉ ከወይን የሆነውን ነገር ሁሉ ከውስጡ ፍሬ ጀምሮ እስከ ገፈፎው ድረስ አይብላ። ራሱን ለመለየት ስእለት ባደረገበት ወራት ሁሉ በራሱ ላይ ምላጭ አይደርስም፤ ለእግዚአብሔር የተለየበት ወራት እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰ ይሆናል፥ የራሱንም ጠጕር ያሳድጋል። ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ባደረገበት ወራት ሁሉ ወደ ሬሳ አይቅረብ። ለአምላኩ ያደረገው ስእለት በራሱ ላይ ነውና አባቱ ወይም እናቱ ወይም ወንድሙ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ሰውነቱን አያርክስባቸው። ራሱን የተለየ ባደረገበት ወራት ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።
ዘኍልቍ 6:1-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገር፦ ወንድ ወይም ሴት ማንኛውም ሰው ራሱን ለእግዚአብሔር በመለየት ናዝራዊ ለመሆን ስእለት ቢያደርግ፥ የወይን ጠጅም ሆነ ማናቸውንም የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣ፤ ከወይን ወይም ከሌላ ነገር የተሠራ ሆምጣጤ ወይም የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣ፤ የወይን ፍሬም ሆነ ዘቢብ አይብላ፤ በናዝራዊነቱ ወቅት ከወይን ሐረግ የሚገኘውን ሁሉ የወይኑን ፍሬ ግልፋፊ ወይም ዘር አይብላ። “ስእለት ተስሎ በናዝራዊነት እስካለ ድረስ ራሱን ምላጭ አይንካው፤ የናዝራዊነት ጊዜው እስኪፈጸም ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ (የተቀደሰ) ይሆናል፤ የራሱንም ጠጒር ያሳድጋል። በናዝራዊነት በአለበት ጊዜ ሁሉ ወደ ሞተ ሰው በድን አይቅረብ፤ ለአምላኩ ያቀረበው የናዝራዊነት ስእለት በራሱ ላይ ስለ ሆነ አባቱ ወይም እናቱ፥ ወንድሙ ወይም እኅቱ ቢሞቱ አስከሬናቸውን በመንካት ራሱን አያርክስ። ናዝራዊ እስከ ሆነ ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ (የተቀደሰ) ነው።
ዘኍልቍ 6:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ለእነርሱ ተናገር፦ ወንድ ወይም ሴት ራሳቸውን ለጌታ ለመለየት የናዝራዊነት ስእለት ቢሳሉ፥ ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን ይለይ፤ ከወይን ወይም ከሚያሰክር መጠጥ የሚሠራን ሆምጣጤ አይጠጣ፥ ማንኛውንም ዓይነት የወይን ዘለላ ጭማቂ አይጠጣ፤ የወይን ዘለላ ወይም ዘቢብ አይብላ። ራሱን በለየበት ወራት ሁሉ ከወይን ጠጅ የሚሠራውን ሌላ ነገር ሁሉ እንዲሁም የውስጡን ፍሬ ወይም ግልፋፊውን እንኳ አይብላ። “ራሱን ለመለየት ስእለት ባደረገበት ወራት ሁሉ በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ ለጌታ የተለየበት ወራት እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰ ይሆናል፥ የራሱንም ጠጉር ያሳድግ። “ለጌታ ራሱን በለየበት ወራት ሁሉ ወደ ሬሳ አይቅረብ። ለአምላኩ ያደረገው ቅድስና በራሱ ላይ ነውና አባቱ ወይም እናቱ ወይም ወንድሙ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ራሱን ስለ እነርሱ አያርክስ። ራሱን በለየበት ወራት ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ነው።