መጽሐፈ ዮዲት 9
9
1ዮዲት ግን በግንባርዋ ተደፍታ በራስዋ ላይ አመድ ነሰነሰች፥ የለበሰችውንም ማቅ ገለጠች፤ በኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ቤት የማታ ዕጣን በሚቀርብበት ጊዜ፥ ዮዲት በታላቅ ድምጽ ወደ ጌታ ጮኸች፤ እንዲህም አለች፦ 2#ዘፍ. 34፥1-31።የአባቴ የስምዖን አምላክ ጌታ ሆይ! የድንግሊቱን ማኅጸን በመፍታት ላረከሱአት፥ ጭኗን በመግለጥ ላሳፈሩአት፥ ማኅጸኗን በማርከስ ላዋረዷት፥ ይበቀል ዘንድ ለመጻተኛ ሰይፍን ሰጠህን፤ አንተ “አይሆንም” ብለህ ነበር፥ እነርሱ ግን አደረጉት። 3ስለዚህም አለቆቻቸውን ለመገደል አሳልፈህ ሰጠህ፥ አልጋቸውም በአታላይነታቸው ኅፍረት ረከስ፥ በደም ተነከረ፥ ባሮቹን ከጌቶቻቸው ጋር፥ ጌቶችንም በዙፋኖቻቸው ላይ መታህ። 4ሚስቶቻቸውን ለንጥቂያ፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለምርኮ አሳልፈህ ሰጠህ፥ ምርኮአቸውን ለተወደዱ ልጆች፥ ለአንተ በቅንዓት ለተቃጠሉ፥ የደማቸው መርከስ ለጠሉ፥ ከዚያም ወደ አንተ ለጮሁት ተከፋፈለ፤ አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ፥ እኔን መበለቲቱን ስማኝ። 5ያለፈውን፥ የአሁኑንና የወደፊቱን አንተ ሠርተሀል፤ አሁን ያለውንና በኋላ የሚመጣውን አንተ ቀርጸሃል፤ አንተ ያሰብከው ሆኗል። 6የዓቀድከው ነገር ከፊትህ ቀርበው “እነሆ መጥተናል” ይላሉ፤ መንገዶችህ ሁሉ የተዘጋጁ ናቸው፥ ፍርድህንም አስቀድሞ የታወቀ ነው። 7እነሆ፥ የአሦር ሰዎች ከሠራዊታቸው ጋር በዝተዋልና፥ በፈረሶቻቸውና በጋላቢዎቻቸው ተመክተዋል፥ በእግረኛ ሠራዊታቸው ተኩራርተዋል፥ በጋሻቸውና በጦራቸው፥ በቀስትና በወንጭፋቸው ታምነዋል፤ ጦርነትን ሰባሪ ጌታ መሆንህን አላወቁም፤ 8ሥምህም ጌታ ነው፤ በክንድህ ኃይላቸውን ስበር፥ በቁጣህ ጥንካሬያቸውን አድቅቅ፤ መቅደስህን ለማርከስ፥ የክቡር ስምህ ማረፊያ የሆነውን ድንኳን ለማሳደፍ፥ የመሠዊያህንም ቀንድ ለመስበር መክረዋልና። 9ትዕቢታቸውን ተመልከት፥ ቁጣህን በላያቸው ላይ ላክ፥ የአሰብሁት እንድፈጽም ለእኔ ለመበለቲቱ ብርቱ እጅን ስጠኝ። 10በአንደበቴ ማታለል ባርያው ከጌታው ጋር፥ ጌታውም ከአገልጋዩ ጋር ምታ፤ ትዕቢታቸውን በሴት እጅ ስበር። 11ብርታትህ በቍጥር፥ ኃይልህም በጠንካራ ሰዎች ላይ አይደገፍምና፤ ነገር ግን የትሑታን አምላክ፥ የታናናሾች ረዳት፥ የደካሞች ድጋፍ፥ ለተገፉ መጠለያ፥ ተስፋ ለቆረጡ አዳኝ ነህ። 12የአባቴ አምላክ፥ የእስራኤል ርስት፥ የሰማይና የምድር ጌታ፥ የውኆች ፈጣሪ፥ የፍጡራን ሁሉ ንጉሥ ሆይ፥ እባክህን እባክህን ጸሎቴን ስማኝ! 13በቃል ኪዳንህ፥ በቤተ መቅደስህ፥ በጽዮን ተራራና ልጆችህ በወረሱት ቤት ላይ የጥፋት ትልሞች የነደፉትን ሁሉ የሚያታልሉ ቃላቶቼ እንዲያቆስላቸውና እንዲያጠፋቸው አድርግ። 14ሕዝቦችህ ሁሉና ነገዶች ሁሉ፥ አምላክ አንተ ብቻ እንደሆንህ፥ ከሁሉም በላይ የኃያልና የብርታት አምላክ፥ ከአንተ በቀር እስራኤልን የሚታደግ ሌላ እንደሌለ እንዲያውቁ አድርግ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዮዲት 9: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ