መጽሐፈ ዮዲት 8
8
ዮዲት
የዮዲት ገለጻ
1በዚያን ጊዜ ስለዚህ ጉዳይ ዮዲት ሰማች፤ እርሷም የሜራሪ ልጅ፥ የዑኽ ልጅ፥ የዮሴፍ ልጅ፥ ዖዚኤል ልጅ፥ የሒልቂያ ልጅ፥ የአናንያ ልጅ፥ የጌድዮን ልጅ፥ የራፋይም ልጅ፥ የአሂቱብ ልጅ፥ የኤልያስ ልጅ፥ የሒልቅያ ልጅ፥ የኤልያብ ልጅ፥ የናትናኤል ልጅ፥ የሳላሚኤል ልጅ፥ የሳራሳዳይ ልጅ፥ የእስራኤል ልጅ ናት። 2ከነገዷና ከወገኗ የሆነው ባሏ ምናሴ፥ በገብስ መከር ጊዜ ሞተ። 3በእርሻ ውስጥ ነዶ ከሚያስሩ ሰዎች ቆሞ ሳለ ራሱን ንዳድ መታው፥ ታምሞ ተኛ፤ በገዛ ሀገሩ በቤቱሊያ ከተማ ሞተ፤ በዶታንና በባላሞን መካከል በሚገኝ እርሻ ውስጥ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት። 4ዮዲትም መበለት ሆና ሦስት ዓመት ከአራት ወር በቤትዋ ተቀመጠች። 5#መሳ. 3፥20፤ 2ነገ. 4፥10።በቤትዋ ጣራ ላይ ለራስዋ ድንኳን ሠራች፥ በወገቧ ማቅ ታጠቀች፥ የመበለትነት ልብስዋንም ለበሰች። 6በሰንበት ዋዜማና በሰንበት፥ በመባቻ ዋዜማና በመባቻ፥ በእስራኤል ቤት በዓላትና የደስታ ቀኖች ካልሆነ በቀር በመበለትነትዋ ጊዜ ሁሉ ትጾም ነበር። 7መልከ መልካምና መልኳም እጅግ የሚያምር ነበረች፤ ባሏ ምናሴም ወርቅና ብር፥ ወንዶች አገልጋዮችና ሴቶች አገልጋዮች፥ ከብቶችንና እርሻዎችን ትቶላት ነበር፤ በእርሱም ትኖር ነበር። 8ፈጽማ እግዚአብሔርን ስለምትፈራ፥ ስለ እርሷ ክፉ የሚናገረ ማንም ሰው አልነበረም።
ዮዲትና አዛውንቶቹ
9ዮዲት ሕዝቡ ውኃ በማጣታቸው ተስፋ ቆርጠው በገዢያቸው ላይ የተናገሩትን ክፉ ነገር፥ እንዲሁም ዑዚያ ከአምስት ቀን በኋላ ከተማይቱን ለአሦራውያን አሳልፎ እንደሚሰጥ ለሕዝቡ በመሐላ የተናገራቸውን ሁሉ በሰማች ጊዜ፥ 10የንብረቷ ሁሉ አስተዳዳሪ የነበረችውን ሴት፥ ዑዚያንን፥ ካብሪስንና ካርሚስን፥ የከተማዋን ሽማግሌዎች እንድትጠራላት ወደ እነርሱ ላከቻት። 11እነርሱም ወደ እርሷ መጡ፥ እርሷም እንዲህ አለቻቸው፦ “የቤቱሊያ ነዋሪዎች ገዢዎች ሆይ ስሙኝ! በዚህ ቀን በሕዝቡ ፊት የተናገራችሁት ንግግር ልክ አይደለም፤ በእግዚብአብሔርና በእናንተ መካከልም ይህን መሐላ አቆማችሁ፥ ጌታ ባይረዳችሁ ከተማይቱን ለጠላቶቻችን አሳልፋችሁ እንደምትሰጡ ተናገራችሁ። 12#ዘዳ. 6፥16፤ ኢዮብ 38፥2።ዛሬ እግዚአብሔርን የምትፈታተኑና በሰዎች መካከል እንደ እግዚአብሔር ሆናችሁ የምትቆሙ እነማናችሁ? 13ሁሉ ቻይ ጌታን እየመረመራችሁት ነው፥ ነገር ግን እስከ ዘለዓለም ምንም አታውቁም። 14#ሮሜ 11፥33፤34፤ 1ቆሮ. 2፥11።የሰው ልብ ጥልቀት ማግኘት አትችሉም፥ በአእምሮው የሚያስበውንም መያዝ አትችሉም፥ ይህን ሁሉ የሠራውን እግዚአብሔርን እንዴት ትመረምራላችሁ? ሐሳቡን ማወቅ ወይም ማስተዋል እንዴት ይሆንላችኋል? ወንድሞቼ ሆይ አይሆንም፥ ጌታ አምላካችንን አታስቆጡት። 15በአምስቱ ቀን ውስጥ ሊረዳን ባይፈልግ እንኳ በፈለገ ጊዜ ሊያድነን ወይም በጠላቶቻችን ፊት ሊያጠፋን ሥልጣን አለው። 16በጌታ አምላካችን ሐሳብ ላይ የማረጋገጫ ዋስትና አታድርጉ፥ ምክንያቱም እግዚአብሔር እንደ ሰው የሚያስፈራሩትና እንደ ሰው ልጅ በመደለያ የሚታለል አይደለም። 17ስለዚህ ማዳኑን በመጠባበቅ ሳለን እንዲረዳን እንጥራው፥ የሚያስደስተው ከሆነ ድምጻችንን ይሰማል።” 18በቀድሞ ዘመን እንደ ተደረገ በትውልዳችን ወይም በእነዚህ ቀኖች፥ ነገድ ወይም ጐሣ ወይም ሕዝብ ወይም ከተማ፥ ከእኛ መካከል በእጅ የተሠሩ አማልክትን ሊያመልክ የተነሣ የለም። 19አባቶቻችን ይህን በማድረጋቸው ነው ለሰይፍና ለብዝበዛ የተሰጡት፥ በጠላቶቻችንም ፊት ብዙ በድን ወደቀ። 20እኛ ግን ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ አናውቅም፥ ስለዚህ እኛን ወይም ወገኖቻችንን እንደማይንቀን ተስፋ እናደርጋለን። 21እኛ ከተያዝን ይሁዳ በሙሉ ትያዛለች፥ መቅደሳችን ቦታችንም ይዘረፋል፥ በመርከሱም ደማችንን ይፈልገዋል። 22የወንድሞቻችን መገደልና የምድሪቱ መያዝ፥ የርስታችንም መጥፋት ባርያዎች በምንሆንበት ሁሉ በአሕዛብ መካከል በራሳችን ላይ ይመለሳል፤ በሚገዙን ፊትም እንቅፋትና ስድብ እንሆናለን። 23ባርነታችን ሞገስን አይሰጠንም፥ ነገር ግን ጌታ አምላካችን ወደ ውርደት ይለውጠዋል። 24ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ፥ ለወንድሞቻችን ምሳሌ እናሳያቸው፥ ሕይወታቸው በእኛ ተደግፏልና፥ የቤተ መቅደሱና የመሠዊያው ኃላፊነት በእኛ ላይ አርፏልና። 25በተጨማሪም አባቶቻችንን እንደ ፈተነ እኛንም ለፈተነን ለጌታ አምላካችን ምስጋና እናቅርብ። 26#ዘፍ. 22፥1-18፤ 29፥1—31፥55።አብርሃም ላይ ያደረገውንና ይስሐቅን እንዴት እንደ ፈተነው፥ በያዕቆብም ላይ በሶርያ መስጴጦምያ የእናቱን ወንድም የላባን በጎች በሚጠብቅበት ጊዜ ምን እንደ ደረሰበት አስታወሱ። 27ልባቸውን ለመመርመር እንዳደረገው እኛን በእሳት አልፈተነንም፥ ወይም አልተበቀለንም፤ እግዚአብሔር ወደ እርሱ የሚቀርቡትን ሊገሥጻቸው ይቀጣቸዋልና። 28ዑዚያ እንዲህ አላት፦ “የተናገርሽውን ሁሉ በጥሩ ልብ ተናገርሽ፥ ቃልሽንም የሚቃወም ማንም የለም። 29ጥበብሽ የተገለጠው ዛሬ ብቻ አይደለም፥ ከድሮ ጀምሮ ከሕይወትሽ መጀመሪያ ጀምሮ አስተዋይነትሽን በሕዝቡ ሁሉ አወቀው፥ የልብሽ ተፈጥሮ ቅን ነውና። 30ነገር ግን በጣም የተጠማው ሕዝብ ቃል የገባነውን እንድንፈፅም አስገደዱን፥ የማንተላለፈውን መሐላ አመጡብን። 31አሁንም አንቺ እግዚአብሔርን የምትፈሪ ሴት ነሽና ጌታ ዝናብ እንዲልክና ጉድጓዳችንን ሁሉ እንዲሞላ ጸልይልን፤ ከዚያ ወዲህም አንዝልም።” 32ዮዲትም እንዲህ አለቻቸው፦ “ስሙኝ፥ በወገኖቻችን ዘንድ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ 33በዚች ሌሊት እናንተ በበሩ ቁሙ፥ እኔም ከአገልጋዬ ጋር እወጣለሁ፤ ከተማይቱን ለጠላቶቻችን አሳልፈን እንሰጣለን ባላችሁባቸው ቀኖች ጌታ በእጄ እስራኤልን ያድናል። 34እናንተ ግን የምሠራውን ለማወቅ አትሞክሩ፥ የምሠራውን እስክፈጽም ድረስ አልነግራችሁምና።” 35ዑዚያና ገዢዎቹም፥ “በሰላም ሂጂ፥ ጌታ እግዚአብሔር ጠላቶቻችንን ለመቀበል በፊትሽ ይሁን” አሏት። 36ከዚህ በኋላ ከድንኳኑ ወጥተው ወደየሥራቸው ሄዱ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዮዲት 8: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ