መጽሐፈ ዮዲት 10
10
ዮዲትና ሆሎፎርኒስ
ዮዲት ወደ ሆሎፎርኒስ ሰፈር ሄደች
1ስለዚህ ዮዲት ወደ እስራኤል አምላክ መጮዃን ከጨረሰች በኋላና እነዚህን ቃላት መናገር ከፈጸመች በኋላ፥ 2ከወደቀችበት ተነሣች፤ አገልጋይቷን ጠርታ በሰንበታትና በበዓላት ቀኖች ወደምትቀመጥበት ቤት ወረደች። 3የለበሰችውን ማቅ አወለቀች፤ የመበለትነት ልብስዋን ተወች፥ ሰውነትዋንም በውኃ ታጠበች፥ ጥሩ ሽቶ ተቀባች፤ ጠጉርዋን አበጠረች፥ በራስዋም ላይ ሻሽ አደረገች፤ ባሏ ምናሴ በሕይወት በነበረበት ጊዜ ትለብሰው የነበረውን የደስታ ልብስዋን ለበሰች። 4ጫማዋን አደረገች፥ አምባርዋን፥ አልቦዋን፥ ቀለበትዋን፥ ጉትቻዋንና ጌጥዋን ሁሉ አደረገች፤ የሚያዩአትን ወንዶች ሁሉ ዐይን ለማማለል እራሷን እጅግ አስዋበች። 5አገልጋይዋን የወይን አቁማዳ፥ የዘይት ማሰሮ አስያዘቻት፤ በከረጢት ውስጥ በሶና የደረቅ በለስ ፍሬ፤ ቂጣ ሞላች፤ ዕቃዎቿን ሁሉ በደንብ ጠቀለለችና አገልጋይዋን አሸከመቻት። 6ወደ ቤቱሊያ ከተማ በር ሄዱ፤ በዚያም ዑዚያንና የከተማይቱን ሽማግሌዎች ካብሪስንና ካርሚስን አገኙአቸው። 7ፊትዋ በጣም ተለውጦ እና የተለየ ልብስ ለብሳ ባዩአት ጊዜ በውበትዋ እጅግ ተደነቁ፤ እንዲህም አሏት፦ 8“ለእስራኤል ልጆች ክብርና ለኢየሩሳሌም ልዕልና የአባቶቻችን አምላክ ሞገስን ይስጥሽ፥ ዕቅድሽንም ያሳካልሽ።” 9እርሷም ለእግዚአብሔር ሰገደች፤ እንዲህም አለቻቸው፦ “ከእኔ ጋር የተነጋገራችሁበትን ነገር ወጥቼ እንድፈጽም የከተማይቱን በር እንዲከፈትልኝ እዘዙ።” እርሷ እንደ ጠየቀችው እንዲከፍቱላት ጐልማሶቹን አዘዙአቸው። 10በከፈቱላትም ጊዜ ዮዲት ወጣች፥ አገልጋይቷም ከእርሷ ጋር፤ የከተማይቱ ሰዎች ተራራውን እስክትወርድና ሸለቆውን አልፋ እስክትሄድ ድረስ ይመለከቷት ነበር፤ ከዚያ በኋላ ግን ሊያዩአት አልቻሉም። 11በቀጥታ በሸለቆው ሄዱ፤ የአሦርያውያን ዘበኞች አገኙአት። 12ያዟትና እንዲህ ሲሉ ይጠይቋት ጀመር፦ “ከማን ወገን ነሽ? ከየት ትመጫለሽ? ወዴትስ ትሄጃለሽ?” እርሷም እንዲህ ስትል መለሰችላቸው፤ “እኔ የዕብራውያን ልጅ ነኝ፥ ለእናንተ መብል እንዲሆኑ ተላልፈው ሊሰጡ ስለሆነ ከእነርሱ ፊት ጠፍቼ መጣሁ። 13እኔ የመጣሁት የሠራዊቶቻችሁ ዋና የጦር አዛዥ የሆነውን ሆሎፎርኒስን ለማግኘትና ለእርሱ እውነተኛ ነገርን ለመንገር ነው፤ ከሰዎቹ አንድም ሳይሞትበት ተራራማውን አገር በሙሉ መያዝ እንዲችል መከተል የሚገባውን መንገድ አሳየዋለሁ”። 14ሰዎቹ ቃሏን በሰሙ ጊዜና ፊትዋንም ባዩ ጊዜ፥ በውበትዋ በዓይናቸው የምትደነቅ ሆና አገኙአት፥ እንዲህም አሏት፦ 15“ወደ ጌታችን ለመቅረብ በፍጥነት ወርደሽ በመምጣትሽ ሕይወትሽን አዳንሽ፤ አሁንም ወደ ድንኳኑ ሂጂ፤ ከእኛ መካከል ጥቂቶቹ ወደ እርሱ ያደርሱሻል፥ በእጁም ያስረክቡሻል። 16በፊቱ በቆምሽ ጊዜ ልብሽ አይፍራ፥ ይህንን ቃልሽን ንገሪው፤ መልካም ያደርግልሻል።” 17ከእርሷና ከአገልጋይዋ ጋር የሚሔዱ መቶ ሰዎች ከእነርሱ መካከል መረጡ፤ ወደ ሆሎፎርኒስ ድንኳንም አደረሱአቸው። 18በየድንኳኑ ስለ ዮዲት መምጣት ተወርቶ ነበርና በሰፈሩ ሁሉ ታላቅ መደነቅ ሆነ፥ መምጣቷንም እስኪነግሩላት ድረስ ከሆሎፎርኒስ ድንኳን ውጭ ቆማ በመጠበቅ ላይ ሳለች ሰዎች በዙሪያዋ ተሰበሰቡ። 19በውበቷ ተደነቁ፥ በእርሷም ምክንያት የእስራኤልን ልጆች አደነቁ፥ እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ፦ “እንዲህ ያሉ ሴቶች ያሉትን ሕዝብ የሚንቀው ማነው? ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳ ማስቀረት መልካም አይደለም፥ ከተውናቸው ምድሪቱን ሁሉ ሊስቡ ይችላሉ።” 20በሆሎፎርኒስ አጠገብ የሚገኙ ጠባቂዎችና አገልጋዮቹ ሁሉ መጥተው ወደ ድንኳኑ አስገቧት። 21ሆሎፎርኒስ በከፋይ፥ በወርቅ፥ መርገድና በከበረ ድንጋይ በተሠራ መጋረጃ ውስጥ በአልጋው ላይ ተጋድሞ ነበር። 22ስለ እርሷ በነገሩት ጊዜ የብር መቅረዝ መብራት በፊቱ ተይዞ ወደ ድንኳኑ ሰፊ ስፍራ መጣ። 23ዮዲት በሆሎፎርኒስና በጦር አለቆቹ ፊት በመጣች ጊዜ፥ በቁንጅናዋ ሁሉም ተደነቁ፤ እርሷም በግንባርዋ ተደፍታ እጅ ነሣችለት፥ አሽከሮቹ ግን አነሷት።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዮዲት 10: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ