መጽሐፈ ዮዲት 7
7
የቤቱሊያ መያዝ
በእስራኤል ላይ የተደረገ ዘመቻ
1በማግሥቱ ሆሎፎርኒስ ወታደሮቹን ሁሉና ሊያግዙት የመጡትን ሰዎች ሁሉ ሠፈራቸውን ለቀው ወደ ቤቱሊያ ጉዞ እንዲጀምሩና የተራራማውን አገር መተላለፊያዎች እንዲይዙ፥ ከእስራኤል ልጆች ጋር ጦርነት እንዲገጥሙ አዘዘ። 2በዚያን ቀን ኃያላን ሰዎቻቸው በሙሉ ከጦር ሰፈራቸው ወጡ፥ ተዋጊዎቹ ቁጥራቸው መቶ ሰባ ሺህ እግረኛና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኛ ጦር ነበረ ይህም ጓዝ የሚጠብቁና እጅግ ብዙ እግረኛ ሰዎች ሳይቆጠሩ ነው። 3ከቤቱሊያ አጠገብ ባለው ሸለቆ ከምንጩ ዳር ሰፈሩ፤ በስፋት ከዶታን እስከ ቤልባይም በርዝመት ደግሞ ከቤቱሊያ በኤስድራሎን ፊት ለፊት እስከሚገኘው እስከ ሳያሞን ድረስ ተስፋፉ። 4የእስራኤል ልጆች ብዛታቸውን በአዩ ጊዜ እጅግ ደነገጡ፥ እርስ በርሳቸውም፦ “አሁን ምድርን ሁሉ ይጨርሱአታል፥ ታላላቅ ተራሮችም ቢሆኑ፥ ሸለቆዎችም ቢሆኑ፥ ኮረብቶች ቢሆኑ ሸክማቸውን መሸከም አይችሉም” ተባባሉ። 5#1መቃ. 12፥28፤29።ሁሉም የጦር መሣሪያቸውን ያዙ፥ በግንቦቻቸው ላይ እሳት አንድደው ሌሊቱን ሙሉ ሲጠብቁ አደሩ። 6በሁለተኛው ቀን ሆሎፎርኒስ በቤቱሊያ በሚገኙ እስራኤላውያን ፊት ፈረሰኞቹን ሁሉ አወጣ። 7የከተማቸውን መግቢያ በሚገባ ሰለለ፤ የውሃ ምንጫቸውን አየና እንዲያዝ አደረገ፥ እንዲጠብቁትም ወታደሮችን አቆመ፥ እርሱ ወደ ሕዝቡ ተመለሰ። 8የኤሳው ልጆች ገዢዎች ሁሉና የሞዓብ ሕዝብ አለቆች ሁሉ እንዲሁም የባሕር ጠረፍ አዛዦች ወደ እርሱ መጡ፥ እንዲህም አሉ፦ 9ጌታ ሆይ በሠራዊትህ ላይ እልቂት እንዳይመጣ የምንነግርህን ስማ፤ 10ይህ ሕዝብ፥ እነዚህ የእስራኤል ልጆች በጦራቸው አይተማመኑም ነገር ግን የሚተማመኑት በሚኖሩባቸው ተራሮች ነው፤ ወደ ተራሮቻቸው ጫፍ መውጣት አይቻልምና። 11ስለዚህ ጌታ ሆይ በሰልፍ ሥርዓት አትዋጋቸው፥ ከአንተ ወገን አንድ ሰው እንኳ አይወድቅም፤ 12አንተ የጦር ሠራዊትህን ይዘህ እዚሁ ሰፈር ቆይ፥ አገልጋዮችህ ከተራራው ሥር የሚመነጨውን የውሃ ምንጭ ይቆጣጠሩ፤ 13ምክንያቱም የቤቱሊያ ነዋሪዎች ውኃ የሚቀዱት ከዚህ ነው፤ ውኃ ጥም ይገድላቸዋል፥ ስለዚህ ከተማቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ፤ በዚያን ጊዜ እኛና ሕዝቡ ወደ ተራራው ጫፍ አጠገብ እንወጣና ከከተማው ማንም ሰው እንዳይወጣ እንጠብቃለን። 14እነርሱ፥ ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸውም በረኃብ ያልቃሉ፥ ሰይፍ ሳይመጣባቸው በሚኖሩባቸው ጎዳናዎች ይወድቃሉ። 15አምጸዋልና በሰላምም አልተቀበሉህምና፥ ክፋትን መልሰህ ትከፍላቸዋልህ። 16ቃላቸው ሆሎፎርኒስንና ሹማምንቱን ደስ አሰኘ፤ እነርሱ እንዳሉት እንዲደረግ አዘዘ፤ 17ስለዚህ የአሞን ልጆች ሠራዊትና ከእነርሱም ጋር አምስት ሺህ አሦራውያንም ሄዱ፥ ሸለቆውንም ሰፈሩ፥ የእራኤላውያንን ውኃቸውንና ምንጮችን ያዙ። 18የኤሳው ልጆችና የአሞን ልጆች ወጥተው በዶታይም ትይዩ ባለው ተራራማ አገር ሰፈሩ፤ ከእነሱም አንዳንዶቹን በሞኹር ወንዝ አጠገብ በኩሲ አቅራቢያ ወዳለው ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ወደ ኤግሬቤ ላኩ፤ የቀሩት የአሦር ወታደሮች ሜዳ ላይ ሰፈሩ፥ ምድርን በሙሉ ሸፈኗት፤ ድንኳኖቻቸውና ጓዛቸው እጅግ ሰፊ ቦታ ያዘ፥ እጅግም ብዙ ሆኑ። 19የእስራኤል ልጆች ወደ ጌታ አምላካቸው ጮኹ፤ መንፈሳቸው ዝላለችና፥ ጠላቶቻቸው ሁሉ ስለ ከበቧቸው፥ ከመካከላቸው ማምለጫ የለምና። 20የአሦር ሠራዊት በሙሉ፥ እግረኞቻቸው፥ ሠረገላዎቻቸውና ፈረሰኞቻቸው ለሠላሳ አራት ቀን ከበቡአቸው፥ የቤቱሊያ ነዋሪዎች በዕቃቸው ያለ ውኃቸው ሁሉ አለቀ፤ 21የውኃ ጉድጓዶችም ደረቁ፥ የሚጠጡት ውኃ ተመጥኖ ይሰጣቸው ስለ ነበር ለአንድ ቀን የሚጠጡት እንኳ አልነበራቸውም። 22ሕፃናቶቻቸው ዛሉ፥ ሴቶችና ወጣቶች በውኃ ጥም አለቁ፥ በከተማይቱ አደባባዮችና በሮቹ ይወድቁ ነበር፥ ምንም ኃይል አልነበራቸውም። 23ሕዝቡ ሁሉ ወጣቶች፥ ሴቶችና ሕፃናት በዑዚያና በከተማይቱ አለቆች አጠገብ ተሰበሰቡ፥ በሽማግሌዎች ሁሉ ፊት በኃይል እንዲህ እያሉ ጮሁ፤ 24“በእኛና በእናንተ መካከል እግዚአብሔር ይፍረድ፤ ከአሦር ልጆች ጋር ሰላም ባለማድረጋችሁ ትልቅ ጉዳት አደረሳችሁብን፤ 25ስለዚህ አሁን የሚረዳን ማንም የለም፤ እግዚአብሔር በውኃ ጥምና በታልቅ ጥፋት በፊታቸው እንድናልቅ በእጃቸው ጥሎናል፤ 26አሁንም ጥሩአቸውና ከተማይቱን በሙሉ እንዲበዘብዙ ለሆሎፎርኒስ ሕዝብና ለሠራዊቱ ሁሉ አሳልፋችሁ ስጧቸው። 27የእነርሱ ምርኮኞች መሆን ይሻለናል፥ ባሮቻቸው መሆናችን አይቀርም፥ ሆኖም በሕይወት እንኖራልን፤ ሕፃናቶቻችን በፊታችን ሲሞቱ፥ ሚስቶቻችንና ወጣቶቻችን የመጨረሻዋን ትንፋሽ ሲተነፍሱ አናይም። 28ሰማይንና ምድርን እንዲሁም የአባቶቻችን ጌታ፥ በኃጢአቶቻችንና በአባቶቻኝ ኃጢአት እየቀጣን ያለውን እግዚአብሔርን እናስመሰክርባችኋለን፤ ዛሬ በዚች ቀን ይህን ነገር እንዳታደርጉ።” 29በጉባኤው መካከል ጽኑ ልቅሶ ሆነ፤ በአንድ ድምፅ ወደ ጌታ እግዚአብሔር ጮኹ። 30ዑዚያም እንዲህ አላቸው “ወንድሞቼ ሆይ አይዟችሁ! አምስት ቀን እንታገስ፤ ጌታ እግዚአብሔር ምሕረቱን ወደ እኛ ይመልሳል፥ እስከ መጨረሻው አይተወንምና። 31ነገር ግን እነዚህ ቀኖች ካለፉ በኋላ እርዳታ ካልመጣልን እናንተ ተናገራችሁት አደርጋለሁ።” 32ሕዝቡንም ወደየሰፈራቸው በተናቸው፤ እነርሱም ወደ ከተማቸው ምሽጐችና ግንቦች ሄዱ፤ ሴቶቹንና ልጆቹን ወደየቤታቸው ሰደዱአቸው፤ በከተማው ውስጥ ታላቅ መከራ#7፥32 ውርደት። ነበር።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዮዲት 7: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ