መጽሐፈ ባሮክ 5

5
1 # ኢሳ. 52፥1፤ 61፥3፤10፤ ራእ. 21፥2። ኢየሩሳሌም ሆይ የኀዘንና የመከራ ልብስሽን አውልቂ፥ ለዘለዓለም ከእግዚአብሔር ክብር የሚወጣውን ውብት ልበሺ። 2ከእግዚአብሔር የሚመጣውን የጽድቅ ካባ ደርቢ፤ የዘላለማዊውን የክብር አክሊል በራስሽ ላይ ድፊ። 3እግዚአብሔር የብርሃንሽን ነጸብራቅ ከሰማይ በታች ላሉ ሁሉ ያሳያልና፤ 4ስምሽ ከእግዚአብሔር ዘንድለዘለዓለም “ሰላም፥ ጽድቅና እግዚአብሔርን የመፍራት ክብር” ተብሎ ይጠራል። 5ኢየሩሳሌም ሆይ ተነሺ! በከፍታ ላይ ቁሚ፤ ወደ ምሥራቅም ተመልከቺ፥ እግዚአብሔር ስላሰባቸው በመደሰት በቅዱሱ ቃል ከምሥራቅና ከምዕራብ የተሰበሰቡትን ልጆችሽን እዪ፤ 6በጠላቶቻቸው ከአንቺ ሲወሰዱ በእግር ነበር፤ እግዚአብሔር ግን እንደ ንጉሥ ዙፋን በክብር ወደ አንቺ ይመልሳቸል። 7እስራኤል በሰላም በእግዚአብሔር ክብር እንዲሄድ፥ እግዚአብሔር ረጃጅም ተራሮች ሁሉና ኮረብታዎች ዝቅእንዲሉ፥ ሸለቆዎች እንዲሞሉ፥ መሬትም እንዲስተካከል አዟልና። 8በእግዚአብሔር ትእዛዝ ጫካዎችና መልካም መዓዛ ያለው ዛፍ ሁሉ እስራኤልን በጥላቸው ጋረዱ። 9እግዚአብሔር እስራኤልን በደስታ፥ በክብሩ ብርሃን፥ ከእርሱ በሚመጣ በምሕረቱና በጽድቁ ይመራቸዋልና።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ