መጽሐፈ መዝሙር 31:7-10

መጽሐፈ መዝሙር 31:7-10 አማ05

ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ፤ መከራዬን አይተህ ጭንቀቴን ታውቃለህ፤ ለጠላቶች አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤ ነገር ግን ሰፊ መንገድ ከፈትክልኝ። እግዚአብሔር ሆይ! በችግር ላይ ስለ ሆንኩ ምሕረትን አድርግልኝ፤ ዐይኖቼ፥ ነፍሴና ሥጋዬ በሐዘን ደክመዋል። ሕይወቴ በሐዘን ዕድሜዬም በመቃተት አለቀ፤ በችግሬ ምክንያት ኀይል አጣሁ፤ አጥንቶቼም ደከሙ።