መዝሙር 31:7-10
መዝሙር 31:7-10 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ፤ መከራዬን አይተህ ጭንቀቴን ታውቃለህ፤ ለጠላቶች አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤ ነገር ግን ሰፊ መንገድ ከፈትክልኝ። እግዚአብሔር ሆይ! በችግር ላይ ስለ ሆንኩ ምሕረትን አድርግልኝ፤ ዐይኖቼ፥ ነፍሴና ሥጋዬ በሐዘን ደክመዋል። ሕይወቴ በሐዘን ዕድሜዬም በመቃተት አለቀ፤ በችግሬ ምክንያት ኀይል አጣሁ፤ አጥንቶቼም ደከሙ።
መዝሙር 31:7-10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አንተ ካገኘችኝ ከዚች መከራዬ መሸሸጊያዬ ነህ፥ ከከበቡኝም ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ። አስተምርሃለሁ፥ በምትሄድባትም በዚች መንገድ አጸናሃለሁ። ዐይኖቼን በአንተ ላይ አጸናለሁ። ወደ አንተ እንዳይቀርቡ በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጕሙአቸው፥ ልብ እንደሌላቸው እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ። የኃጥኣን መቅሠፍታቸው ብዙ ነው፤ በእግዚአብሔር የሚታመኑትን ግን ይቅርታ ይከባቸዋል።
መዝሙር 31:7-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በምሕረትህ ደስ እሰኛለሁ፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤ መከራዬን አይተሃልና፤ የነፍሴንም ጭንቀት ዐውቀሃል። ለጠላት አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤ ነገር ግን እግሮቼን ሰፊ ቦታ ላይ አቆምሃቸው። እግዚአብሔር ሆይ፤ በመከራ ውስጥ ነኝና ማረኝ፤ ዐይኖቼ በሐዘን ደክመዋል፤ ነፍስና ሥጋዬም ዝለዋል። ሕይወቴ በመጨነቅ፣ ዕድሜዬም በመቃተት ዐለቀ፤ ከመከራዬ የተነሣ ጕልበት ከዳኝ፤ ዐጥንቴም በውስጤ ሟሟ።