ትንቢተ ኤርምያስ 33:14-17
ትንቢተ ኤርምያስ 33:14-17 አማ05
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለእስራኤልና ለይሁዳ ሕዝብ የተስፋ ቃል የምፈጽምበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ በዚያን ጊዜ የዳዊት ዘር ቅርንጫፍ የሆነ አንድ ጻድቅ ንጉሥ እመርጣለሁ፤ ያም ንጉሥ በአገሪቱ ላይ ቅን የሆነውን ነገር ያደርጋል፤ ትክክለኛ ፍርድም ይሰጣል። የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ከጠላት እጅ ድነው በሰላም ይኖራሉ። ከተማይቱም ‘እግዚአብሔር ጽድቃችን ነው’ ተብላ ትጠራለች፤ ከዳዊት ዘር በእስራኤል ላይ የሚነግሥ ንጉሥ ከቶ እንደማይጠፋ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤

