ኤርምያስ 33:14-17
ኤርምያስ 33:14-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“እነሆ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የሰጠሁትን መልካም የተስፋ ቃል የምፈጽምበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር። በዚያም ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት የጽድቅን ቍጥቋጥ አበቅልለታለሁ፤ እርሱም ፍርድንና ጽድቅን በምድር ያደርጋል። በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል፤ ኢየሩሳሌምም ተዘልላ ትቀመጣለች፤ የምትጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው። እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከዳዊት ዘንድ አይታጣም።
ኤርምያስ 33:14-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ ‘ለእስራኤል ቤትና ለይሁዳ ቤት የገባሁትን የተስፋ ቃል የምፈጽምበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል እግዚአብሔር። “ ‘በዚያ ዘመንና በዚያ ጊዜ፣ ከዳዊት ቤት ጻድቅ ቅርንጫፍ አበቅላለሁ፤ በምድሪቱም ፍትሕንና ጽድቅን ያደርጋል። በዚያ ዘመን ይሁዳ ይድናል፤ ኢየሩሳሌም ያለ ሥጋት ትኖራለች፤ የምትጠራበትም ስም፣ “እግዚአብሔር ጽድቃችን” የሚል ይሆናል።’ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘ከዳዊት ዘር በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ፈጽሞ አይታጣም፤
ኤርምያስ 33:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እነሆ፥ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የተናገርሁትን መልካም ቃል የምፈጽምበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር። በዚያም ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት የጽድቅን ቍጥቋጥ አበቅልለታለሁ፥ እርሱም ፍርድንና ጽድቅን በምድር ያደርጋል። በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል ኢየሩሳሌምም ተዘልላ ትቀመጣለች፥ የምትጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው። እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከዳዊት ዘንድ አይታጣም፥
ኤርምያስ 33:14-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለእስራኤልና ለይሁዳ ሕዝብ የተስፋ ቃል የምፈጽምበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ በዚያን ጊዜ የዳዊት ዘር ቅርንጫፍ የሆነ አንድ ጻድቅ ንጉሥ እመርጣለሁ፤ ያም ንጉሥ በአገሪቱ ላይ ቅን የሆነውን ነገር ያደርጋል፤ ትክክለኛ ፍርድም ይሰጣል። የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ከጠላት እጅ ድነው በሰላም ይኖራሉ። ከተማይቱም ‘እግዚአብሔር ጽድቃችን ነው’ ተብላ ትጠራለች፤ ከዳዊት ዘር በእስራኤል ላይ የሚነግሥ ንጉሥ ከቶ እንደማይጠፋ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤
ኤርምያስ 33:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
“እነሆ፥ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የተናገርሁትን መልካም ቃል የምፈጽምበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ። በዚያም ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት የጽድቅን ቁጥቋጥ አበቅልለታለሁ፤ እርሱም ፍርድንና ጽድቅን በምድር ያደርጋል። በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል ኢየሩሳሌምም በደኅንነት ትቀመጣለች፤ እርሷም፦ ‘ጌታ ጽድቃችን ነው’ በሚለው ስም ትጠራለች። ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ዳዊት በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ፈጽሞ አያጣም፤