ኦሪት ዘጸአት 33:19-23
ኦሪት ዘጸአት 33:19-23 አማ05
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ደግነቴን ሁሉ በፊትህ አሳልፋለሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ስሜን በፊትህ ዐውጃለሁ፤ የምምረውን እምራለሁ፤ የምራራለትንም እራራለታለሁ፤ ፊቴን አይቶ ለመኖር የሚችል ሰው ስለሌለ ፊቴን ለማየት አትችልም። ነገር ግን እዚህ በአጠገቤ በአለት ላይ የምትቆምበት ስፍራ አለ። የእኔ ክብር በዚያ ሲያልፍ በአለቱ ስንጣቂ አቈይሃለሁ፤ እስካልፍ ድረስ በእጄ እጋርድሃለሁ፤ ከዚያም በኋላ እጄን አነሣለሁ፤ አንተም ፊቴን ሳይሆን ጀርባዬን ታያለህ።”

