ኦሪት ዘዳግም 32:9-12
ኦሪት ዘዳግም 32:9-12 አማ05
እስራኤል የእግዚአብሔር ድርሻ ነው፤ ያዕቆብም አንጡራ ሀብቱ ነው። “በነፋሻማ ባዶ በረሓ በምድረ በዳ አገኘው፤ መከታ ሆነለት፤ ጠበቀውም፤ እንደ ዐይን ብሌኑም ተንከባከበው። በጫጩቶችዋ ላይ እንደምታንዣብብ፥ ጎጆዋን እንደምትጠብቅ ንስር፥ እርሱን ለመያዝ ክንፎቹን ይዘረጋል፤ በክንፎቹም ጫፍ ይደግፈዋል። እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ ባዕድ አምላክ ከእርሱ ጋር አልነበረም።

