ዘዳግም 32:9-12
ዘዳግም 32:9-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሕዝቡ ያዕቆብም የእግዚአብሔር ዕድል ፋንታ ሆነ፤ እስራኤልም የርስቱ ገመድ ነው። በምድረ በዳ አጠገባቸው፤ በጥማትና በድካም ቦታ፥ በውድማ ከበባቸው፤ መገባቸው፤ መራቸውም፤ እንደ ዐይን ብሌንም ጠበቃቸው። ንስር ጫጩቶቹን በክንፎቹ በታች እንደሚሰበስብ፥ በጎኑም እንደሚያቅፍ፥ በክንፎቹ አዘላቸው፤ በደረቱም ተሸከማቸው። እግዚአብሔር ብቻውን መራቸው፤ ከእነርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም።
ዘዳግም 32:9-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የእግዚአብሔር ድርሻ የገዛ ሕዝቡ፣ ያዕቆብ የተለየ ርስቱ ነውና። እርሱን በምድረ በዳ፣ ባዶና ጭው ባለ በረሓ ውስጥ አገኘው፤ ጋሻ ሆነው፤ ተጠነቀቀለትም፤ እንደ ዐይኑ ብሌን ጠበቀው። ንስር ጐጆዋን በትና፣ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትረብብ፣ እነርሱን ለመያዝ ክንፎቿን እንደምትዘረጋ፣ በክንፎቿም እንደምትሸከማቸው፣ እግዚአብሔር ብቻ መራው፤ ምንም ባዕድ አምላክ ዐብሮት አልነበረም።
ዘዳግም 32:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ሕዝቡ ነው፤ 2 ያዕቆብም የርስቱ ገምድ ነው። በምድረ በዳ በጥማት፥ 2 የነፋስ ጩኸትም በሞላበት ውድማ አገኘው፤ 2 ከበበው ተጠነቀቀለትም፤ 2 እንደ ዓይን ብሌን ጠበቀው። ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ፥ 2 በእነርሱም ላይ እንደሚሰፍፍ፥ 2 ክንፎቹን ዘርግቶ ወሰዳቸው፥ 2 በክንፎቹም አዘላቸው። እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ 2 ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም።