ኦሪት ዘዳግም 25:13-16

ኦሪት ዘዳግም 25:13-16 አማ05

“ትልቅና ትንሽ ሚዛን ወይም መስፈሪያ በመያዝ ሰውን አታጭበርብር። እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ለረጅም ዘመን ትኖር ዘንድ እውነተኛና ታማኝ የሆነ ሚዛንና መስፈሪያ ብቻ ይኑርህ፤ እግዚአብሔር አምላክህ እንደዚህ አድርገው በማጭበርበር ተንኰል የሚሠሩትን ሰዎች ሁሉ ይጠላል።