ዘዳግም 25:14-16
ዘዳግም 25:14-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በቤትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ መስፈሪያ አይኑርልህ። አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ እውነተኛና ፍጹም ሚዛን ይሁንልህ፤ እውነተኛና ፍጹም መስፈሪያም ይሁንልህ። ይህን የሚያደርግ ሁሉ፥ ክፋትንም የሚያደርግ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና።
ያጋሩ
ዘዳግም 25 ያንብቡዘዳግም 25:14-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በቤትህም ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት የተለያዩ መስፈሪያዎች አይኑሩህ። አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፣ ጻድቅና የታመነ ሚዛንና መስፈሪያ ይኑርህ። አምላክህ እግዚአብሔር እንዲህ ያሉትን ነገሮች የሚፈጽመውንና የሚያምታታውን ሁሉ ይጸየፈዋልና።
ያጋሩ
ዘዳግም 25 ያንብቡዘዳግም 25:14-16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በቤትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ የሆነ ሁለት ዓይነት መስፈሪያ አይኑርልህ። ይህን የሚያደርግ ሁሉ ክፋትንም የሚያደርግ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጣላ ነውና አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ እውነተኛና ፍጹም ሚዛን ይሁንልህ፤ እውነተኛና ፍጹም መስፈሪያም ይሁንልህ።
ያጋሩ
ዘዳግም 25 ያንብቡ