ምሳሌ 27:4-10

ምሳሌ 27:4-10 NASV

ንዴት ጨካኝ፣ ቍጣም ጐርፍ ነው፤ በቅናት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል? የተገለጠ ዘለፋ፣ ከተደበቀ ፍቅር ይሻላል። ከጠላት ደጋግሞ መሳም ይልቅ፣ የወዳጅ ማቍሰል ይታመናል። ለጠገበ ማር አይጥመውም፤ ለተራበ ግን እሬት እንኳ ይጣፍጠዋል። ከቤቱ ወጥቶ የሚባዝን ሰው፣ ጐጆዋን ለቅቃ እንደምትባዝን ወፍ ነው። ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤ የወዳጅ ማስደሰትም ከቅን ምክሩ ይመነጫል። የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ አትተው፤ መከራ በሚያጋጥምህ ጊዜ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፤ ሩቅ ካለ ወንድም ቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}