ምሳሌ 1:20-23

ምሳሌ 1:20-23 NASV

ጥበብ በጐዳና ላይ ጮኻ ትጣራለች፤ በየአደባባዩ ድምፅዋን ከፍ ታደርጋለች፤ ዉካታ በበዛባቸው ጐዳናዎች ላይ ትጮኻለች፤ በከተማዪቱም መግቢያ በር ላይ እንዲህ ትላለች፤ “እናንተ አላዋቂዎች፤ ማስተዋል የሌለበት መንገዳችሁን እስከ መቼ ትወድዱታላችሁ? ፌዘኞች በፌዝ ደስ የሚሰኙት፣ ሞኞችስ ዕውቀትን የሚጠሉት እስከ መቼ ነው? ዘለፋዬን ብትሰሙኝ ኖሮ፣ ልቤን ባፈሰስሁላችሁ፣ ሐሳቤንም ባሳወቅኋችሁ ነበር።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}