ዘሌዋውያን 8:30-36

ዘሌዋውያን 8:30-36 NASV

ቀጥሎም ሙሴ በመቅቢያው ዘይትና በመሠዊያው ላይ ካለው ደም ጥቂት ወስዶ፣ በአሮንና በልብሱ እንዲሁም በአሮን ልጆችና በልብሳቸው ላይ ረጨ፤ በዚህም ሁኔታ አሮንንና ልብሱን፣ ልጆቹንና ልብሳቸውን ቀደሰ። ሙሴም አሮንና ልጆቹን እንዲህ አላቸው፤ “ሥጋውን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቀቅሉት፤ በዚያም፣ ‘አሮንና ልጆቹ ይብሉት’ ተብዬ በታዘዝሁት መሠረት፣ በክህነት መስጫው መሥዋዕት መሶብ ውስጥ ካለው ቂጣ ጋራ ብሉት፤ የተረፈውንም ሥጋና ቂጣ በእሳት አቃጥሉ። የክህነት መቀበያችሁ ሥርዐት እስከሚፈጸምበት እስከ ሰባት ቀን ድረስ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቈዩ፤ ሥርዐቱንም ለመፈጸም ሰባት ቀን ይወስዳልና። ዛሬ የተፈጸመው ይህ ሥርዐት ለእናንተ ማስተስረያ እግዚአብሔር ያዘዘው ነው። እንዳትሞቱ ሰባቱን ቀንና ሌሊት ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትለዩ፤ የእግዚአብሔርንም ሥርዐት ጠብቁ፤ የታዘዝሁት እንዲህ ነውና።” አሮንና ልጆቹም እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ።