እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አሮንንና ልጆቹን፣ ልብሰ ተክህኖውን፣ የመቅቢያ ዘይቱን፣ ለኀጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን፣ ሁለቱን አውራ በጎችና ቂጣ ያለበትን መሶብ አምጣ፤ ማኅበሩን በሙሉ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሰብስብ።” ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ማኅበሩም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ተሰበሰበ። ሙሴም ማኅበሩን፣ “እግዚአብሔር እንዲደረግ ያዘዘው ይህ ነው” አላቸው። ሙሴም አሮንንና ልጆቹን ወደ ፊት አወጣቸው፤ በውሃም ዐጠባቸው። አሮንን እጀ ጠባብ አለበሰው፤ መቀነት አስታጠቀው፤ ቀሚስ አጠለቀለት፤ ኤፉድ ደረበለት፤ በልዩ ጥበብ በተጠለፈው መታጠቂያ ኤፉዱን አስታጠቀው፤ በላዩም አሰረው፤ የደረት ኪሱን በላዩ አደረገለት፤ በደረት ኪሱም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን አኖረ። እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት፣ ሙሴ መጠምጠሚያውን በአሮን ራስ ላይ አደረገ፤ በመጠምጠሚያው ላይ በፊት ለፊቱ በኩል የተቀደሰውን የወርቅ አክሊል አደረገለት።
ዘሌዋውያን 8 ያንብቡ
ያዳምጡ ዘሌዋውያን 8
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዘሌዋውያን 8:1-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች