BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች预览

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

28天中的第4天

የእግዚአብሔር የትላንት ታማኝነት ስለ ነገ ተስፋ እንዲኖረን ምክንያት ይሆንልናል። ነገን በተስፋ ለመጠባበቅ፣ ትላንት እግዚአብሔር ምን ያህል ታማኝ እንደሆነ ማስታወስ እንችላለን። ያኔ ታማኝ ከነበረ፣ ለምን ዳግመኛ ታማኝ አይሆንም?

ያንብቡ፦

ዕብራውያን 10÷23

ምልከታዎን ያስፍሩ፡

እግዚአብሔር ለእርስዎና ለማህበረሰብዎ ፍቅሩን የገለጠበትን ሶስት የተለያዩ መንገዶች ያስታውሱ።

ስለእግዚአብሔር ታማኝ ፍቅር ያልዎት ትውስታዎች ዛሬ ላይ እንዴት ተስፋ ይሰጥዎታል?

ምልከታዎን ከእግዚአብሔር ጋር ወደሚደረግ ውይይት ይቀይሯቸው። ታማኝ ፍቅሩ ለእርስዎ ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዲሁም ደግሞ የእግዚአብሔርን ታማኝነት በምን መልኩ ዛሬ ላይ ማየት እንደሚፈልጉ ይናገሩ።

读经计划介绍

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።

More