1
የማርቆስ ወንጌል 13:13
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
Thelekisa
Phonononga የማርቆስ ወንጌል 13:13
2
የማርቆስ ወንጌል 13:33
ጊዜው መቼ እንዲሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፤ ጸልዩም።
Phonononga የማርቆስ ወንጌል 13:33
3
የማርቆስ ወንጌል 13:11
ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፥ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።
Phonononga የማርቆስ ወንጌል 13:11
4
የማርቆስ ወንጌል 13:31
ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።
Phonononga የማርቆስ ወንጌል 13:31
5
የማርቆስ ወንጌል 13:32
ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም።
Phonononga የማርቆስ ወንጌል 13:32
6
የማርቆስ ወንጌል 13:7
ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፥ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው።
Phonononga የማርቆስ ወንጌል 13:7
7
የማርቆስ ወንጌል 13:35-37
እንግዲህ በማታ ቢሆን ወይም በእኩለ ሌሊት ወይም ዶሮ ሲጮኽ ወይም በማለዳ ቢሆን ባለቤቱ መቼ እንዲመጣ አታውቁምና ድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ስለዚህ ትጉ። ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ።
Phonononga የማርቆስ ወንጌል 13:35-37
8
የማርቆስ ወንጌል 13:8
ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ በልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል፤ ራብ ይሆናል፤ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
Phonononga የማርቆስ ወንጌል 13:8
9
የማርቆስ ወንጌል 13:10
አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል።
Phonononga የማርቆስ ወንጌል 13:10
10
የማርቆስ ወንጌል 13:6
ብዙዎች፦ እኔ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፥ ብዙዎችንም ያስታሉ።
Phonononga የማርቆስ ወንጌል 13:6
11
የማርቆስ ወንጌል 13:9
እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል በምኵራብም ትገረፋላችሁ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ።
Phonononga የማርቆስ ወንጌል 13:9
12
የማርቆስ ወንጌል 13:22
ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ያስቱ ዘንድ ምልክትና ድንቅ ያደርጋሉ።
Phonononga የማርቆስ ወንጌል 13:22
13
የማርቆስ ወንጌል 13:24-25
በዚያን ወራት ግን ከዚያ መከራ በኋላ ፀሐይ ይጨልማል ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ።
Phonononga የማርቆስ ወንጌል 13:24-25
Ekuqaleni
IBhayibhile
Izicwangciso
Iividiyo