1
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:17-18
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና። እንደዚህ አድርጎ ክርስቶስን የሚያገልግል እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል፤ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው።
Thelekisa
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 14:17-18
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:8
በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 14:8
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:19
እንግዲህ የሰላም ነገርና እርስ በርሳችንም የምንታነጽበትን ነገር እንከተል።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 14:19
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:13
እንግዲህ ከዚህ በኋላ አንዳችን በአንዳችን ላይ አንፍረድ፤ ነገር ግን ከመፍረድ ይልቅ ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖርበት ይወስን።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 14:13
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:11-12
“እኔ ሕያው ነኝ፤” ይላል ጌታ፤ “ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ልሳንም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል፤” ተብሎ ተጽፎአልና። እንግዲያስ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 14:11-12
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:1
በእምነት የደከመውንም አከራካሪ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሳትፈርዱበት ተቀበሉት።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 14:1
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:4
አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን ጌታ ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 14:4
Ekuqaleni
IBhayibhile
Izicwangciso
Iividiyo