1
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:2
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
መልካም፥ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
Primerjaj
Razišči ወደ ሮሜ ሰዎች 12:2
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:1
እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ሰውነታችሁን ሕያው መሥዋዕት፥ ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ አድርጋችሁ እንድታቀርቡ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም መንፈሳዊ አገልግሎታችሁ ነው።
Razišči ወደ ሮሜ ሰዎች 12:1
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:12
በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤
Razišči ወደ ሮሜ ሰዎች 12:12
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:21
ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።
Razišči ወደ ሮሜ ሰዎች 12:21
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:10
እርስ በእርሳችሁ በወንድማማችነት መዋደድ አጥብቃችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ይበልጥ ተከባበሩ፤
Razišči ወደ ሮሜ ሰዎች 12:10
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:9
ፍቅር እውነተኛ ይሁን፤ ክፉውን ነገር ተጸየፉ፥ መልካም የሆነው ነገር አጥብቃችሁ ያዙ፤
Razišči ወደ ሮሜ ሰዎች 12:9
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:18
ቢቻላችሁ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።
Razišči ወደ ሮሜ ሰዎች 12:18
8
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:19
“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ፤ ይላል ጌታ” ተብሎ ተጽፎአልና፥ ተወዳጆች ሆይ! ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ለቁጣው ቦታ ስጡ እንጂ።
Razišči ወደ ሮሜ ሰዎች 12:19
9
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:11
ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ጌታን አገልግሉ፤
Razišči ወደ ሮሜ ሰዎች 12:11
10
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:3
እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችሁ እንደሰጣችሁ እምነት መጠን፥ በረጋ አእምሮ አስቡ እንጂ ማሰብ ከሚገባችሁ በላይ ራሳችሁን ከፍ አድርጋችሁ እንዳታስቡ በተሰጠኝ ጸጋ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ እናገራለሁና።
Razišči ወደ ሮሜ ሰዎች 12:3
11
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:17
ለማንም በክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን ነገር አስቡ።
Razišči ወደ ሮሜ ሰዎች 12:17
12
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:16
እርስ በርሳችሁ በአንድ ነገር ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፤ ነገር ግን የተናቁትን ቅረቡ። በራሳችሁ ዐዋቂዎች ነን አትበሉ።
Razišči ወደ ሮሜ ሰዎች 12:16
13
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:20
ነገር ግን ጠላትህ ቢርበው አብላው፤ ቢጠማው አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።
Razišči ወደ ሮሜ ሰዎች 12:20
14
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:14-15
የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ።
Razišči ወደ ሮሜ ሰዎች 12:14-15
15
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:13
ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ተቀበሉ።
Razišči ወደ ሮሜ ሰዎች 12:13
16
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:4-5
በአንድ አካል ብዙ የሰውነት ክፍሎች እንዳሉን፥ የሰውነት ክፍሎቹም ሥራ አንድ እንዳልሆነ ሁሉ፥ እንዲሁም ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በእርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው የሰውነት ክፍሎች ነን።
Razišči ወደ ሮሜ ሰዎች 12:4-5
Domov
Sveto pismo
Bralni načrti
Videoposnetki